Monday, September 23, 2024
spot_img

የአፍሪካ ኅብረት የሰብዓዊና የሕዝብ መብቶች ኮሚሽን በትግራይ ጦርነቱን ያስጀመረው መከላከያ ነው አለ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ሰኔ 11፣ 2013 ― የአፍሪካ ሕብረት የሰብዓዊና የሕዝብ መብቶች ኮሚሽን ይህን ያለው በኢትዮጵያ ያለውን ሁኔታ እየተከታተለ መሆኑን ባሳወቀበት ወቅት ነው።

ኮሚሽኑ ጥቅምት 24፣ 2013 የፌዴራል መንግሥቱ የመከላከያ ሠራዊት በሕወሃት ኃይሎች ላይ ወታደራዊ እርምጃ መክፈቱን ተከትሎ በዚያኑ እለት በአጸፋው ሕወሃት ሰሜን እዝን አጥቅቷል ነው ያለው።

በጥቅምት ወር በትግራይ ለተቀሰቀሰው ጦርነት መነሻ ሆኗል በሚል የሚነሳውን የሰሜን እዝ ጥቃትን አስመልክቶ የፌዴራል መንግሥቱ ሕወሃት ቀድሞ ጥቃት መሰንዘሩን በወቅቱ ማሳወቁ አይዘነጋም።

በዚያኑ ሰሞን በድምጺ ወያኔ ቴሌቪዥን የቀረቡትና በጦርነቱ የሞቱት የሕወሃት አመራሩ ሴኮ ቱሬ መብረቃዊ ሲሉ የገለጹትን እርምጃ በአገር መከላከያ ሠራዊት ላይ መውሰዳቸውን ተናግረው ነበር።

ሆኖም ኋላ ላይ አሁን ከመንግሥት ጋር እየተዋጉ እንደሚገኙ የሚናገሩት ሌላኛው የሕወሃት አመራር አቶ ጌታቸው ረዳ፣ የሴኮን ንግግር የሚያጥፍ ንግግር ሲያደርጉ ተደምጠዋል።

የአፍሪካ ኅብረት ያወጣውን ያወጣውን መረጃ በሚመለከት በመንግሥት በኩል የተሰጠ ምላሽ የለም።

ነገር ግን ከሰሞኑ የኢትዮጵያ መንግስት የአፍሪካ ሕብረት የሰብዓዊና የሕዝብ መብቶች ኮሚሽን በትግራይ ክልል የተናጠል ምርመራ አደርጋለሁ ማለቱን እንደሚቃወም ገልጾ ነበር።

መንግሥት ኅብረቱ ምርመራ ማድረግ ከፈለገ ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ጋር በጋራ ማካሄድ ይችላል ብሏል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img