Monday, September 23, 2024
spot_img

ሸኔ በምዕራብ ወለጋ ሁለት በማዕድን ሥራ ላይ የነበሩ የአፍጋኒስታን ዜጎችን ማገቱን አስታወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ሰኔ 10፣ 2013 ― መንግሥት ኦነግ ሸኔ የሚለውና ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት በሚል ሥያሜ የሚጠራው ታጣቂ ኃይል በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ በማዕድን ማውጣት ላይ የነበሩ ሁለት የአፍጋኒስታን ዜጎችን ማገቱን የታጣቂዎቹ ቃል አቀባይ ነው የሚባለው ኦዳ ተርቢ መግለጹን የሚያመለክቱ መረጃዎች ወጥተዋል።

ታጣቂ ኃይሉ ያዝኳቸው ያላቸው ሁለቱ የአፍጋኒስታን ዜጎች ሰዒድ አቡበከር እና ሰዒድ ሐሺም እንደሚሰኙና ለደቡብ አፍሪካው ሙን ሮክ ለተባለ ኩባንያ የሚሠሩ መሆናቸውንም ታጣቂ ኃይሉ አሳውቋል።

የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ ሦስት ቻይናዊያን የማዕድን ሠራተኞችን በአካባቢው በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልጾ የነበረ ሲሆን፣ ኋላ ላይ እነዚህን ቻይናዊያን ለቀይ መስቀል አስረክቦ ማኅበሩ ደግሞ ለአገሪቱ ኤምባሲ ማስተላለፉ ተዘግቦ ነበር።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img