Sunday, October 6, 2024
spot_img

በመጪው ሰኞ ምርጫ የሚከናወንባቸው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ ብዛት 445 መሆኑ ታወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ሰኔ 9፣ 2013 ― በመጪው ሰኞ በሚደረገው አገር አቀፉ ምርጫ ትግራይ ክልል ከያዘው 38 መቀመጫ ውጭ ከአጠቃላዩ የፓርላማ መቀመጫ ምርጫው የሚከናወንባቸው የተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ ብዛት 445 መሆኑን ምርጫ ቦርድ አሳውቋል፡፡

በአሁኑ አገር አቀፍ ምርጫ በአጠቃላይ 509 የፓርላማ መቀመጫዎች እንዳሚገኙ የጠቆመው ምርጫ ቦርድ፣ ቀሪዎቹ 64 የሐዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫዎች ድምጽ የሚሰጥባቸው ጳጉሜ 1፣ 2013 መሆኑን ነው ይፋ ያደረገው፡፡

ስልሳ አራት የምርጫ ክልሎች ከሰኔ 14ቱ ምርጫ ውጪ ከተደረጉባቸው ምክንያቶች መካከል፤ በጸጥታ እና በሌሎች ችግሮች ምክንያት የመራጮች ምዝገባ አለመከናወን አንዱ መሆኑን ምርጫ ቦርድ ገልጿል። የድምጽ መስጫ ወረቀቶች ኅትመት ላይ የተፈጠረ እክል እንዲሁም ቦርዱ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ያሉት የፍርድ ቤት ሙግቶችም በምክንያትነት ከተጠቀሱት ውስጥ ይገኙበታል።

እንደ ቦርዱ መረጃ ከሆነ ከስልሳ አራቱ የፓርላማ መቀመጫዎች መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆኑቱ የሚወክሉት የሶማሌ እና የደቡብ ክልሎችን ነው። ሰኔ 14 ሙሉ ለመሉ ምርጫ የማይካሄድበት የሶማሌ ክልል በ23 የፓርላማ መቀመጫዎች ዝርዝሩን የሚመራ ሲሆን፤ ደቡብ ክልል በ16 መቀመጫዎች ይከተላል።

የአማራ ክልል መራጮች ለ10 የፓርላማ መቀመጫዎች ሰኔ 14 ድምጽ የማይሰጡ ሲሆን፤ በኦሮሚያ ክልል ደግሞ 7 የተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫዎች በተመሳሳይ ሁኔታ ለምርጫ አይቀርቡም። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 4 የፓርላማ መቀመጫዎች በሰኔ 14ቱ ምርጫ አልተካተቱም።

እንደ ሶማሌ ሁሉ ሙሉ ለሙሉ ምርጫ በማካይሄድበት ሐረሪ ክልል፤ 2 የተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫዎች ላይ ሰኞ ዕለት ድምጽ አይሰጥም። በአፋር ክልልም 2 የፓርላማ መቀመጫዎች ተመሳሳይ ዕጣ ፈንታ እንደገጠማቸውም የኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘገባ ያመለክታል፡፡

የፎቶ ምንጭ፡ የኢትዮጵያ ኢንሳይደር ድረ ገጽ

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img