Sunday, September 22, 2024
spot_img

አምነስቲ ኢንተርናሽናል የአቶ ዳውድ ኢብሳ የመንቀሳቀስ መብት እንዲከበር ጠየቀ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ሰኔ 9፣ 2013 ― ዓለም አቀፍ የመብቶች ተሟጋቹ አምነስቲ ኢንተርናሽናል በቁም እስር ላይ የሚገኙት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ሊቀመንበሩ አቶ ዳውድ ኢብሳ በቁም እስር ላይ መገኘታቸው አንደሚያሳስበው ለሰላም ሚኒስትሯ ሙፈሪሃት ካሚል በጻፈው ደብዳቤ አመልክቷል፡፡

አቶ ዳውድ ኢብሳ ከሚያዝያ 25፣ 2013 አንስቶ በቤታቸው በቁም እስር ላይ እንደሚገኙ የጠቆመው አምነስቲ፣ ፖሊስ ቤታቸው ገብቶ ብርበራ በማድረግ ላፕቶፕ እና ስልክ መውሰዱን እንዲሁም ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ባለው ጊዜ ቤታቸው ማንም ሰው ዝር እንዳይል መከልከሉንም አሳውቋል፡፡

አምኔስቲ እንዳለው ከሆነ ፖሊስ ይህን ተግባር የፈጸመው ያለምንም ሕጋዊ ማዘዣ በመሆኑ የፖለቲከኛው የመንቀሳቀስ መብት ተጥሷል፡፡

አምነስቲ በደብዳቤው አሁንም ቢሆን አቶ ዳውድ ኢብሳ በአስቸኳይ ከቁም እስሩ ነጻ እንዲወጡ የጠየቀ ሲሆን፣ ይህ የማይደረግ ከሆነ ደግሞ በቂ ማስረጃ ካለ ፖሊስ በፖለቲከኛው ላይ ክስ ሊመሠርት እንደሚገባ ነው ያመለከተው፡፡

በተጨማሪም አቶ ዳውድ ምግብ እና ሌሎች የሚፈልጓቸው ነገሮች እንዲቀርብላቸውም አምነስቲ ለወይዘሮ ሙፈሪሃት በጻፈው ደብዳቤ ጠይቋል፡፡

ሊቀመንበሩ በቁም እስር ላይ የሚገኙበት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር በርካታ አመራር እና አባላቶቼ በመንግሥት በመታሠራቸው በምርጫ መሳተፍ ይቸግረኛል በማለት፣ በመጪው ሰኞ ከሚካሄደው አገራዊ ምርጫ ውጭ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img