Sunday, September 22, 2024
spot_img

ምርጫ ቦርድ የድምጽ መስጫ ወረቀቶችን ወደ ክልሎች ማጓጓዝ መጀመሩ ተሰማ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ሰኔ 8፣ 2013 ― የፊታችን ሰኞ ሰኔ 14 ለሚካሄደው ምርጫ የሚያገለግሉ የድምጽ መስጫ ወረቀቶች ከትላንት አመሻሽ ጀምሮ ወደ ምርጫ ክልሎች መሰራጨት እንደጀመሩ ተሰምቷል፡፡

በምርጫው የድምጽ አሰጣጡ የሚካሄደው በ44 ሺሕ 372 የምርጫ ጣቢያዎች እንደሆነ ትላንት በሰጡት መግለጫ የገለፁት የምርጫ ቦርድ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ ሶልያና ሽመልስ፣ ‹‹ቦርዱ እስካሁን ሲያጓጉዝ የቆየው ለምርጫ አስፈጻሚዎች ስልጠና የሚውሉ ሰነዶችን እንዲሁም ከፍተኛ ጥንቃቄ የማይጠይቁ እንደ ማሸጊያ ሳጥን አይነቶቹን ቁሳቁሶችን ሲሆን የድምጽ መስጫ ወረቀቶችን ወደ ምርጫ ክልሎች ማጓጓዙ ዛሬ ምሽት ይጀምራል›› ብለው ነበር፡፡

‹‹የድምጽ መስጫ ወረቀት ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚጠይቅ ስለሆነ፤ ቀኑ [ለምርጫ] በተጠጋ ቁጥር ማድረስ ስላለብን ነበር እስካሁን የዘገየነው›› በሚል አስረድተው እንደነበር የዘገበው አዲስ ዘይቤ ድረ ገጽ ነው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img