Sunday, October 6, 2024
spot_img

በየመን የጀልባ መስጠም አደጋ በርካታ ስደተኞች ሳይሞቱ እንዳልቀረ ተነገረ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ሰኔ 8፣ 2013 ― በየመን ላህጅ ግዛት የሚገኙ ዓሳ አጥማጆች በራስ አል አራ አቅራቢያ ከሚገገኘው ውሃ 25 አስከሬኖችን ማግኘታቸውን ለአዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ገልጸዋል፡፡

አንድ የክልሉ ባለሥልጣን እንደተናገሩት ከ 160 እስከ 200 የሚደርሱ ሰዎችን የያዘ ጀልባ ከሁለት ቀናት በፊት በአካባቢው ተገልብጧል፡፡

ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት አይኦኤም በርካታ ቁጥር ያላቸው ስደተኞችን የያዘ መርከብ መስጠሙን የሚያረጋግጡ ዘገባዎችን እያጣራሁ ነው ብሏል፡፡

አደን አል ጋድ የተባለ አንድ የየመን የዜና አውታር በበኩሉ እስከ 150 የሚደርሱ ስደተኞች መስጠማቸውን ከምንጮቹ ማግኘቱን ጠቁሞ አራት የመናውያን እንደሚገኙበትም አስታውቋል።

ራስ አል-አራ የመን እና ጅቡቲን የሚለይ እና የቀይ ባህርን ከባህረ ሰላጤው ጋር የሚያገናኝ 20 ኪሎ ሜትር ስፋት ያለው ሲሆን፣ ከባብ አል ማንዳብ በስተምሥራቅ ያለው አካባቢ የሰዎች አዘዋዋሪዎች የሚጠቀሙበት የባህር ዳርቻ መሆኑን የቢቢሲ ዘገባ ያለመክታል፡፡

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በመቶዎች የሚቆጠሩ ከአፍሪካ ቀንድ በተለይም ከኢትዮጵያና ሶማሊያ የመጡ ስደተኞች ወደ ሳዑዲ አረቢያ ለመግባት መስመሩን አቋርጠው ወደ የመን ይሻገራሉ፡፡

ብዙዎቹ የህገ ወጥ ሰው አዘዋዋሪዎቹ ጀልባዎች ከመጠን በላይ የተጨናነቁ እና ለውሃው ተስማሚ ያልሆኑ በመሆናቸው ጉዞው በአደጋ የተሞላ ነው፡፡

በሚያዝያ ወር በህገ-ወጥ አዘዋዋሪዎች የምትተዳደር ጀልባ ከየመን ወደ ጅቡቲ በመጓዝ ላይ ሳለች ተገልብጣ ቢያንስ 44 ስደተኞች መሞታቸውን ዘገባው አስታውሷል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img