Friday, October 11, 2024
spot_img

በምሥራቅ ናይል ተፋሰስ ጉባኤ ላይ ግብጽ ሳትሳተፍ ቀረች

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ሰኔ 8፣ 2013 ― የምሥራቅ ናይል ተፋሰስ ጉባኤ አባል የሆኑት ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ደቡብ ሱዳን በአዲስ አበባ እየተወያዩ ይገኛሉ፡፡

ግብጽ የጉባኤው አባል ብትሆንም በአገሪቱ በኩል የተገኘ ሚንስትርም ሆነ ተወካይ ባለሞያ አለመሳተፉ ታውቋል፡፡

የዚህ ጉባኤ ዋና አላማ የምሥራቅ ናይል ተፋሰስ ውሀ ሚንስትሮች ተፋሰሱን ማልማት በሚያስችሉ አጀንዳዎች ዙሪያ መወያየት እና በሚያጋጥሙ ችግሮች ዙሪያ የጋራ መፍትሄ ማስቀመጥ እንደሆነ በጉባኤው መክፈቻ ላይ የኢትዮጵያ ውሃ እና መስኖ ሚንስትሩ ዶክተር ስለሺ በቀለ ተናግረዋል መባን የዘገበው አል ዓይን ነው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img