Friday, October 11, 2024
spot_img

ከምርጫ ቦርድ ውጪ የተመሰረቱ የምርጫ ጣቢያዎች ጳጉሜ 1 ይመርጣሉ ተባለ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ሰኔ 7፣ 2013 ― ከምርጫ ቦርድ ዕውቅና ውጪ እንደተመሠረቱ የተገለጹት 79 የምርጫ ጣቢያዎች የተመዘገቡ መራጮች ስድስተኛው አጠቃላይ የመጀመሪያው ምርጫ በሚደረግበት ሰኔ 14፣ 2013 መርሃ ግብር ድምጽ እንደማይሰጡ ተገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የኮሙዩኒኬሽንስ አማካሪ ሶልያና ሽመልስ ዛሬ በዲ ሊዮፖል ሆቴል በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቁት፣ እነዚህ የምርጫ ጣቢያዎች ጳጉሜን 1፣ 2013 ለድምጽ መስጫ በተያዘው ሁለተኛ መርሃ ግብር ወቅት ድምጽ ይሰጣሉ ተብሏል፡፡

ይኼ የሚሆንበትም ምክንያት ቦርዱ ያለዕውቅናው የተከፈቱት የምርጫ ጣቢያዎች የመዘገቧቸው መራጮች ነዋሪ መሆናቸው መረጋገጥ ስለሚኖርበትና ተጨማሪ ማጣሪያ ማድረጉ ጊዜ ስለሚጠይቅ እንደሆነም ሶልያና ተናግረዋል፡፡ ምንም እንኳን እነዚህን የምርጫ ጣቢያዎች ቦርዱ ባያውቃቸውም የተመዘገቡት መራጮች ግን ይኼ መረጃ ስለሌላቸውና የመምረጥ መብታቸው መከበር ስለሚኖርበት፣ ተጨማሪ ማጣሪያ ከተደረገ በኋላ ጳጉሜን 1፣ 2013 ድምጽ እንዲሰጡ ይደረጋል ተብሏል፡፡

በጠቅላላው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ካለው 547 መቀመጫዎች መካከል 59 መቀመጫዎችን የሚያስመርጡ የምርጫ ክልሎች ሰኔ 14፣ 2013 ድምጽ አያሰጡም፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img