Friday, October 11, 2024
spot_img

እነ እስክንድር ነጋ ያለመከሰስ መብታቸውን ተረጋግጦ ከእስር እንዲፈቱ በጠበቆቻቸው የቀረበው አቤቱታ ውድቅ ተደረገ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ሰኔ 7፣ 2013 ― የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ ፀረ ሽብር ችሎት እነ እስክንድር ነጋ በስድስተኛው አገራዊ ምርጫ እጩ ሆነው በመቅረባቸው ምክንያት ያለመከሰስ መብታቸውን ፍርድ ቤቱ አረጋግጦ ከእስር እንዲፈቱ በጠበቆች የቀረበው አቤቱታ ላይ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡

በዛሬው እለት የተሰየመው ችሎቱ በተከሳሾች ላይ የወንጀል ክሱ የተመሠረተው እጩ ሆነው ከመመዝገባቸው በፊት ስለሆነ ጥያቄውን አልተቀበልኩትም በማለት በእስር ላይ ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ ብሏል፡፡

የተከሳሾቹ ጠበቆች በብይኑ ላይ ቅሬታ አለን በማለት ለጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ለማቅረብ በማዘጋጀት ላይ መሆናቸውን ፓርቲው አስታውቋል፡፡ ያለመከሰስ መብታቸው በፍርድ ቤቱ ተረጋግጦ በጠበቆቻቸው እንዲፈቱ ተጠቅቆ የነበረው የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ሊቀመንበር አቶ እስክንድር ነጋን ጨምሮ ስንታየሁ ቸኮል፣ ቀለብ ሥዩም እና አስካለ ደምሌ ናቸው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img