Friday, October 11, 2024
spot_img

አሕመዲን ጀበል ራሳቸውን ከምርጫ አገለሉ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ሰኔ 7፣ 2013 ― የዛሬ ሳምንት ሰኔ 14፣ 2013 ለሚካሄደው አገራዊ ምርጫ ላይ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በግል ለመወዳደር በእጩነት የተመዘገቡት አሕመዲን ጀበል ከምርጫው ራሳቸውን ማግለላቸውን በማኅራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ አሳውቀዋል፡፡

በኦሮሚያ ክልል ጂማ ዞን ለመወዳደር ተመዝገበው የነበሩት አሕመዲን፣ ሰባት ቀናት ከቀሩት ምርጫ ራሳቸውን ያገለሉት በግል ምክንያት እንደሆነ ነው የገለጹት፡፡

አሕመዲን ጀበል በተለይ ከኢትዮጵያ ሙስሊሞች የመብት እንቅስቃሴ እንዲሁም ከታሪክ ነክ መጻሕፍት ዝግጅት ጋር በተገናኘ በሥፋት ይታወቃሉ፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img