Friday, November 22, 2024
spot_img

አብን እና መኢአድን ጨምሮ አምስት ፓርቲዎች ምርጫው በችግሮች የተሞላ ነው አሉ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ሰኔ 7፣ 2013 ― የዛሬ ሳምንት ሰኞ ሰኔ 14፣ 2013 በመጀመሪያ ዙር ይካሄዳል ተብሎ ቀጠሮ የተያዘለት አገራዊ ምርጫ ‹‹በብዙ ችግሮች እና ወጣ ውረዶች የተሞላ›› ነው ሲሉ በሰጡት መግለጫ ላይ ገልጸዋል፡፡

አብን፣ ህብር ኢትዮጵያ፣ እናት ፓርቲ፣ ባልደራስ፣ እና መኢአድ ፓርቲ የተካተቱበት ስብስብ ምንም እንኳን ምርጫው ችግር ቢኖርበትም ራሳቸውን ከምርጫው እንደማይገልሉ አስታውቋል፡፡

በዚሁ መግለጫ ላይ የፓርቲዎቹ አመራሮች በሂደቱ ላይ ገጥሞናል ያሉትን ዘርዝረዋል፡፡ ፓርቲዎቹ ችግሮቹ በምዝገባ ሂደት ላይ እንደነበሩ ጠቁመው፣ ‹‹ቅስቀሳ ስናደርግ መታየታችን የተሳሳተ ስእል ሰጥቷል›› ብለዋል፡፡ መግለጫውን የሰጡትም ‹‹የማሳወቅ ኃላፊነት ስላለብን ነው›› የሚል ምክንያት አስቀምጠዋል፡፡

ከፓርቲዎቹ አመራሮች መካከል የአብን ሊቀመንበር አቶ በለጠ ሞላ እንደተናገሩትም ፓርቲዎቹ ራሳቸውን ከምርጫው የማያገሉት ‹‹ይሄ አገር ብዙ ነገር መሸከም ይጠይቃል፤ ከዛ አንጻር እያደረግነው እንደሆነ ግንዛቤ ሊወሰድ ይገባል›› ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

በዚሁ መግለጫ ወቅት ‹‹የምርጫውን ውጤት ምንም ይሁን ምን ትቀበላላችሁ ወይ›› በሚል ለቀረበው ጥያቄ፤ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ሊቀመንበር አቶ በለጠ ሞላ፤ በዚህ ጉዳይ ላይ ፓርቲዎች ‹‹ብያኔያቸውን›› የሚሰጡት የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱን እና ቆጠራውን ከተመለከቱ በኋላ ነው ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። ‹‹ውጤት መቀበል አለመቀበል በአጠቃላይ ሂደት ድምር ግምገማ ላይ ተመስርተን የምናደርገው ነው የሚሆነው›› ሲሉም አስረድተዋል፡፡

በሌላ በኩል አንዳንድ ክልሎች ሙሉ በሙሉ በራቸውን ዘግተዋል ያሉት አቶ በለጠ ሞላ፣ በተለይ የኦሮሚያ ክልል ሙሉ ለሙሉ ለፓርቲዎች ዝግ ነው ብለዋል፡፡

ከዚሁ ጋር በተገናኘ የአማራ ክልልን የሚያስተዳድረው የአማራ ብልጽግና፣ የኦሮሚያ ብልጽግና በሩን ዘግቶ ብቻውን ከፍተኛ መቀመጫ ካገኘ ‹‹አናሳ ልሆን እችላለሁ በሚል›› ዘግይቶም ቢሆን በነርሱ ላይ ‹‹ወከባና እንግልት እየፈጸመብን ነው›› ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ፎቶ፡ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img