Wednesday, October 9, 2024
spot_img

አሜሪካ በኢትዮጵያ ቴሌኮም ጨረታ ላሸነፈው ጥምረት ገንዘብ አለመልቀቋ ተሰማ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ሰኔ 7፣ 2013 ― በቅርቡ በኢትዮጵያ ቴሌኮም አገልግሎት ለመስጠት ጨረታ ላሸነፈው ግሎባል ፓርትነርሺ ፎር ኢትዮጵያ የገንዘብ ድጋፍ ያደርጋል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረው የአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ኮርፖሬሽን የሚጠበቀውን ገንዘብ አለመልቀቁ ተሰምቷል፡፡

ጨረታውን ያሸነፈው የጥምረቱ አካል የሆነው የቮዳኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሻሚል ጆሱብ እንደተናገሩት ስምምነቱ ገና በሒደት ላይ ነው፡፡

ሆኖም ጥምረቱ በኢትዮጵያ ገበያ ላይ መግባቱንና ያስቀመጠውን የጨረታ ገንዘብም ለመንግስት ገቢ ማድረጉን ከቀናት በፊት በወዳጅነት ፓርክ በተካሄደ ሥነ ሥርዐት ይፋ ማደረጉ አይዘነጋም፡፡

ይለቀቃል ተብሎ የነበረው ይኸው ፈንድ አሜሪካ በቅርቡ በኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ላይ የቪዛ እቀባ መጣሏ ስጋት ውስጥ እንዲወድቅ አድርጎታል ነው የተባለው፡፡

የአሜሪካን የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማራመድና ለማሳለጥ ዓላማ ይዞ በፈረንጆቹ በ2019 የተቋቋመው ዓለም አቀፍ የልማት ኮርፖሬሽን፣ ቀድሞ ለጥምረቱ 500 ሚሊዮን ዶላር ማቅረቡ ነበር የተሰማው፡፡

ይህ ተቋም በዋናነት ቻይና እና ሩሲያ በአፍሪካ ያላቸውን ጉልህ ተጽእኖ በማዳከም፣ ከተቻለም መገደብና በአሜሪካ የውጭ ፖሊሲ ፍላጎት መተካት እንደሆነ በድረ ገጹ ላይ ያስቀመጠ ነው፡፡

ወደ ኢትዮጵያ ቴሌኮም ገበያ የገባው ግሎባል ፓርትነርሺፕ የተባለው ጥምረት በውስጡ የእንግሊዙን ቮዳፎን፣ የደቡብ አፍሪካውን ቮዳ ኮም፣ የኬንያውን ሳፋሪ ኮም፣ የጃፓኑን ሱሚቱሞና የእንግሊዝ መንግሥትን የፋይናንስ ተቋም ሲዲሲና የአሜሪካ አቻውን የያዘ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img