Thursday, October 10, 2024
spot_img

ግብጽ እና ሱዳን ኢትዮጵያ ግድቡን ለመሙላት የጀመረችውን ጉዞ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ያስቁምልን አሉ

እንዲጠቀሙበት ተጠየቀ አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ሰኔ 3፣ 2013 ― የግብፅ የውጭ ጉዳይ እና መስኖ ሚኒስትሮች በሱዳን ባደረጉት የአንድ ቀን ይፋዊ ጉብኝት፣ ከሱዳን አቻዎቻቸው ጋር መገናኘታቸውን ተከትሎ የጋራ መግለጫ አውጥተዋል፡፡

አገራቱ በመግለጫቸውም የሕዳሴ ግድቡን ጉዳይ በተመለከተ ሁለገብ ስምምነት ላይ ለመድረስ ‹‹ኢትዮጵያ በቁም ነገር፣ በታማኝነት እና በእውነተኛ የፖለቲካ ፍላጎት እንድትደራደር በቀጣና፣ በአህጉር እና በዓለም አቀፍ ደረጃዎች ግፊት እንዲደረግ ሁለቱ ሀገራት በጋራ እንደሚሰሩ›› አስታውቀዋል፡፡ በዚህም በሕዳሴው ግድብ ሙሌት እና አስተዳደር ላይ ‹‹ፍትሃዊ እና ህጋዊ አስገዳጅ ስምምነት እንዲደረስ እንደሚሰሩ›› ገልጸዋል፡፡

ሁለቱ ሀገራት ‹‹የኢትዮጵያ ፖሊሲ የሚያስከትለውን አደጋ ለመከላከል የአለም አቀፉ ማህበረሰብ ንቁ ጣልቃ ይግባ›› ብለዋል።

በቀጠናው እና በአፍሪካ አህጉር ፀጥታ፣ ሰላም እና መረጋጋትን ለማስጠበቅ፣ ‹‹የግብፅ እና የሱዳን ቅንጅት አስፈላጊነት›› ላይ መስማማታቸውንም የሚያትተው መግለጫው፣ ለዚህም ‹‹ኢትዮጵያ በግድቡ ጉዳይ የያዘችውን ፖሊሲ መቀጠሏ የሚያስከትለውን አደጋ ለመከላከል የአለም አቀፉን ማህበረሰብ ንቁ ጣልቃ ገብነትን ይጠይቃል›› ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያ በመጪው የክረምት ወቅት ‹‹የሕዳሴውን ግድብ ለመሙላት የጀመረችውን ጉዞ ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ እንዲያስቆም›› ነው በመግለጫቸው የጠየቁት፡፡

አስገዳጅ ስምምነት ሳይደረስ የግድቡን ሁለተኛ ዙር ሙሌት ማከናወን እንደሚያሰጋቸውም ሁለቱ ሀገራት በድጋሚ ገልጸዋል፡፡

ሁለቱን አገራት የመጉዳት ፍላጎት እንደሌላት በተደጋጋሚ የገለጸችው ኢትዮጵያ፣ አስገዳጅ ስምምነት የመፈረም ፍላጎት እንደሌላትና የግድቡን ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌትም በተያዘው ጊዜ እንደምታከናውን ቁርጠኛ አቋም መያዟ ይታወቃል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img