Thursday, October 10, 2024
spot_img

ትዊተር ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሚሚ ዓለማየሁን የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል አደረገ

እንዲጠቀሙበት ተጠየቀ አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ሰኔ 3፣ 2013 ― ትውልደ ኢትዮጲያዊቷ ሚሚ ዓለማየሁ የትዊተር ዳይሬክተሮች አባል ሆና መመረጧን ትዊተር አስታውቋል፡፡

የዓለማችን ግዙፉ የማኅበራዊ ሚዲያ ተቋም ትዊተር ድርጅቱ በገለልተኛ እና በጠንካራ ግለሰብ እንዲመራ ትውልደ ኢትዮጵያዊቷን ሚሚ ዓለማየሁን የቦርድ ዳይሬክተሮች አባል አድርጎ መምረጡን ነው የገለጸው፡፡

ሚሚ ከ20 ዓመታት በላይ በምጣኔ ሐብትና በኢንቨስትመንት መስኮች ልምድ ያላት ባለሙያ መሆኗ ለድርጅቱ የወደፊት ጉዞ ከፍተኛ አቅም እንደሚፈጥርም አመልክቷል።

የትዊተርን አለም አቀፍ ተደራሽነቱንም በማስፋት ረገድ ሚሚ በዘርፉ ያላት ልምድ ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ ነው የተነገረው።

ከሹመቱ በኋላ ሚሚ በትውተር ገጿ ‹‹ትዊተር አለም አቀፍ ተደራሽነቱን ለማስፋፈት በሚንቀሳቀስበት በዚህ ወቅት በኋላፊነት በመስራቴ በጣም ደስተኛ ነኝ፣ ከቦርድ አመራሮች ጋር ስኬታማ ስራዎችን ለመስራት ተዘጋጅቻለሁ›› ስትል አስፍራለች፡፡

ሚሚ ዓለማየሁ በአሜሪካ ከፍተኛ ተቋማት ላይ ላለፉት 20 ዓመታት በፋይናንስ መስክ በልዩ ልዩ ኃፊነቶች ያገለገለች ሲሆን፣ በፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ የስልጣን ዘመን በአሜሪካ የልማት ተቋም ስር በሚገኘው የኦቨርሲ ኢንቨስተመንት ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ በመሆኑ ሰርታለች።

በኢትዮጵያ የተወለደችውና የአሜሪካ ዜግነት ያላት ሚሚ ዓለማየሁ ሁለተኛ ዲግሪዋን ያጠናቀቀችው በዓለም አቀፍ ንግድ እና ዓለም አቀፍ ሕግ የተማረች መሆኗን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img