Thursday, October 10, 2024
spot_img

አሜሪካ በትግራይ ክልል ለአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ የ181 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ይፋ አደረገች

እንዲጠቀሙበት ተጠየቀ አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ሰኔ 3፣ 2013 ― የአሜሪካ ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት በትግራይ ክልል ለአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ የሚውል የ181 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ይፋ አድርጓል፡፡

ድጋፉ በክልሉ አስቸኳይ ጊዜ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው 3 ሚሊዮን ዜጎች እንደሚውልም ድርጅቱ አስታውቋል፡፡

የምግብ፣ የንጹህ መጠጥ፣ መጠለያ፣ የጤና አገልግሎትን ጨምሮ መሰረታዊ አገልግቶችን ለማቅረብ እንደሚያስችልም የአሜሪካ ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት ኃላፊ ሳማንታ ፓወር ገልጸዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም ለአርሶ አደሮች ዘርና ማዳበሪያን ጨምሮ የግብርና ግብአትን ለማቅረብ ይውላልም ነው የተባለው፡፡

በተጨማሪም ድጋፉ ለማኅበራዊና ስነ ልቦናዊ ጫና ማገገሚያ ፕሮግራም እንደሚውልም የድርጅቱ መረጃ ያመላክታል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img