አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ሰኔ 2፣ 2013 ― መንግሥትና የዴሞክራሲ ኃይሎች ከቀናት በኋላ የሚካሄደውን ምርጫ ውጥረቶችን ለማርገብ እንዲጠቀሙበት በአውሮፓ ኅብረት ፓርላማ የሰብአዊ መብቶች ንዑስ ኮሚቴ ሰብሳቢዋ ማሪያ አሬና ጠይቀዋል።
በአውሮፓ ፓርላማ ላይ በተነበበው መግለጫቸው በአገሪቱ የቀጠለው ብሔር ተኮር ግጭት እጅጉን እንደሚያሳስባቸው የገለጹት ማሪያ አሬና፣ የኢትዮጵያውያን ስቃይ ሊገታ እንደሚገባም ነው ያመለከቱት።
መንግስትም የዜጎችን ሰብአዊ መብቶች እንዲከበሩ ግዴታ እንዳለበት የገለጹ ሲሆን፣ ተፈናቃዮች ባሉባቸው አካባቢዎችም ያልተገደበ የሰብአዊ አቅርቦት እንዲኖር ማድረግ አለበት ነው ያሉት።
የአውሮፓ ኅብረት ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ የኢትዮጵያ መንግሥት የዜጎችን የሰብአዊ መብቶች እንዲጠብቅና ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች ለተፈናቀሉ ያልተገደበ ሰብአዊ አቅርቦት እንዲኖር መጠየቁ የሚታወስ ነው።