አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ሰኔ 2፣ 2013 ― የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሜህ ሹክሪ እና የውሃ ሀብትና መስኖ ሚኒስትር ሞሐመድ አብደል አቲ ከሱዳን ባለስልጣናት ጋር ለመመካር ካርቱም ገብተዋል።
አል ዐይን ኒውስ እንደዘገበው ሚኒስትሮቹ ካርቱም ሲደርሱ የሱዳን የውጭ ጉዳይ እና የውሃና መስኖ ሚኒስትሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
በካርቱም በሚኖራቸው ቆይታም ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ እየገነባች ባለው የሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ትኩረት አድርገው ይመክራሉ ነው ተባለው።
ሚኒስትሮቹ በካርቱም ቆይታቸው ከሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ሊቀመንበር ሌተናል ጄኔራል አብደል ፈታህ አል-ቡርሃን እና ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብደላ ሀምዶክ ጋር እንደሚመክሩም ተነግሯል።