Thursday, October 10, 2024
spot_img

በርካታ የትግራይ አካባቢዎች በረሃብ አፋፍ ላይ መሆናቸውን አንቶንዮ ጉቴሬዝ ገለጹ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ሰኔ 1፣ 2013 ― በርካታ የትግራይ አካባቢዎች በረሃብ አፋፍ ላይ መሆናቸው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ዋና ጸሃፊ አንቶንዮ ጉተሬዝ ተናግረዋል፡፡

ዋና ጸሐፊው የትግራይ ሁኔታ በዚህ ከቀጠለ እጅግ አስከፊ ወደ ሆነ ደረጃ መሸጋገሩ አይቀሬ ነው ሲሉ አሳስበዋል፡፡

የተጋረጠውን የረሃብ አደጋ ለመግታት ሰብአዊ እርዳታ ማዳረስ እንዲሁም በቂ ፈንድ ማድረግ እንደሚያስፈልግም ዋና ጸሐፊው በትዊተር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልእክት አስታውቋል፡፡

‹‹አሁን የሚከናወኑ ተግባራት ለበርካታ ሰዎች የመኖርና አለመኖር ጉዳይ መሆናቸውን መረዳት ተገቢ ነው›› ሲሉም ነው የተመድ ዋና ጸሐፊው የገለጹት፡፡

የጉተሬዝ ትግራይን የተመለከተ መግለጫ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በትግራይ ያሉ የግጭቱ ተዋናዮች ተኩስ እንዲያቆሙና ያልተገደበ የስብአዊ እርዳታ ተደራሽነት እንዲኖር ጥሪ እያደረገ ባለበት ወቅት ነው፡፡

የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ እየተካሄደ ባለው ግጭት ሳቢያ በትግራይ ያለው የሰብዓዊ ቀውስ አሳሳቢ መሆኑንና በኢትዮጵያ ከ40 ዓመት ወዲህ ከፍተኛ የረሀብ አደጋ እንዳንዣበበ ባለፈው ሳምንት ማስታወቁ የሚታወስ ነው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img