Thursday, October 10, 2024
spot_img

የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የሕወሃት ንብረት እጃቸው ላይ የሚገኝ ግለሰሰቦች ጥቆማ እንዲያደርጉ ጠየቀ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ሰኔ 1፣ 2013 ― የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በሽብርተኝነት የተፈረጀው የሕወሃት አባላት ንብረት በኪራይ፣ በውክልና፣ በአደራ፣ በጠባቂነት ወይም በሌላ ማንኛውም መንገድ ይዘው የሚገኙ ሰዎች ጥቆማ እንዲያደርጉ ጠይቋል፡፡

ዐቃቤ ሕግ የሕወሃት ቡድን አባላት የሆኑ ንብረቶችን በኪራይ፣ በዉክልና፣ በአደራ፣ በጠባቂነት ወይም በሌላ ማንኛውም መንገድ ይዘው እያለ ሪፖርት የማያደርጉ አካላት በሽብር አዋጁና አግባብነት ባላቸዉ ሌሎች ሕጎች ተጠያቂ እንደሚሆኑም አስጠንቅቋል፡፡

ሕወሃት በመከላከያ ሠራዊት የሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት ፈጸመ ከተባለበት ጊዜ አንስቶ በቡድኑና አባላቱ ላይ የወንጀልና የሃብት ምርመራዎች ሲያከናውን መቆየቱን ያስታወሰው ዐቃቤ ሕግ፣ ከዚሁ ጋር በተያያዘ በወንጀል የተገኘ እና በአገር ዉስጥ ወይም በውጭ አገር የተደበቀ ሀብት ላይ ጥቆማ እንዲቀርብ ጥሪ ባደረገው መሰረት ከሕዝብ የተሰጡ ብዛት ያላቸው ጥቆማዎችና መረጃዎችን መሰረት በማድረግ የድርጅቱንና አባላትን ሐብት ጨምሮ በተደረገው የማጣራት ሥራ በርካታ ውጤቶች መመዝገባቸውን ጨምሮ አስታውቋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img