Thursday, October 10, 2024
spot_img

በማይካድራ በተፈጸመው ጥቃት ቢያንስ 767 ሰዎች መገደላቸውን የሚያመልክት ሪፖርት ይፋ ሆነ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ሰኔ 1፣ 2013 ― በምእራብ ትግራይ ማይካድራ ከተማ በተፈጸመው ጥቃት ቢያንስ 767 ሰዎች መገደላቸውን ማጣራቱን ሬውተርስ ይዞት በወጣውና አዲስ ባለው ጥናት ይፋ አድርጓል፡፡

የዜና ተቋሙ ይህንኑ ይፋ ባደረገበት ሪፖርቱ በማይካድራ ከጥቃቱ መጀመሪያ አንስቶ ተፈጽሟል ስላለው ክስተት ሰፋ ያለ ማብራሪያ አስነብቧል፡፡

ሬውተርስ በሪፖርቱ ጥቅምት 24 በፌዴራል መንግሥት እና በሕወሃት መካከል የተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ የአማራ ብሔር ተወላጆችን ለመጠበቅ በሚል ፋኖ 2 ሺሕ አባላት ከፌዴራል መንግሥት ጎን መሰለፋቸውን ከፋኖ አባል አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡

ቅዳሜ ጥቅምት 28፣ 2013 እነዚህ የመንግሥት ኃይሎች ከማይካድራ 65 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ ክፍለ ጦር ደርሰዋል የተባለ ሲሆን፣ በዚህ ወቅት እዚያው ሥፍራ የፋኖ ታጣቂዎች የትግራይ ተወላጆችን መኖር የምትፈልጉ ከሆነ ቤታችሁን ለቃችሁ ውጡ እያሉ በእሳት ማያያዛቸውን ሬውተርስ ሰባት የትግራይ ተወላጆች እንደነገሩት ገልጧል፡፡ ሆኖም አሁን በአካባቢው የተሾሙት ኃላፊ ግን በሥፍራው ቤቶቹ የተቃጠሉት ከሕወሃት ታጣቂዎች ጋር በነበረ ውጊያ ወቅት ነው ብለውኛል ሲል አስነብቧል፡፡

በቀጣይ ቀን ከማይካድራ በ45 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው አብዱራፊም ነዋሪዎች በኤርትራ በኩል መከበባቸው የተገለጸ ሲሆን፣ ይህንኑ ተከትሎም በተከታዩ ቀን 46 ሰዎች ሲገደሉ፣ ከ200 በላይ ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል፡፡

ኋላም ጥቃቱ ወደ ማይካድራ እየተቃረበ መምጣቱ ሲሰማ፣ በማይካድራ የሚገኙ የትግራይ ተወላጅ የሆኑ ወጣቶች እና ሚሊሻዎች ራሳችንን ለመከላከል በሚል መታጠቅ እንደጀመሩ ሪፖርቱ አመልክቷል፡፡ በአካባቢው የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ግን እነዚህ የታጠቁ ሰዎች በአብዛኛው አጎራባች ካለው ሳምረ ከሚባል ሥፍራ መምጣታቸውን ተናግረዋል፡፡

ሰኞ ጥቅምት 30፣ 2013 ማለዳ ላይ ቢላዋ እና ቆንጨራ ከታጠቁ ወጣቶች መካከል አንዳንዶቹ በማካድራ የሰዎችን መታወቂያ ሲያጣሩ እንደነበርና ከጥቂት ቆይታ በኋላም የብዙ ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈውን ጥቃት መፈጸማቸውን በሪፖርቱ ላይ ሰፍሯል፡፡

ሬውተርስ በማይካድራ ከሞቱት 767 ሰዎች ባሻገር፣ በዚሁ ሪፖርት ላይ በትግራይ ጦርነት ሰበብ በአጠቃላይ ከ8 ሺሕ በላይ ሰዎች መገደላቸውን በቤልጅየም ጌንት ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር ከሆኑት የን ኒይሰን መስማቱን የዘገበ ሲሆን፣ ከነዚህ መካከል 2 ሺሕ 562 ሰዎች ማንነት ተረጋግጧል ነው ያለው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img