Sunday, September 22, 2024
spot_img

ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኖቤል ሽልማት የሰጠው ኮሚቴ ኃላፊነቱን እንዲለቅ ተጠየቀ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ሰኔ 1፣ 2013 ― በፈረንጆቹ 2019 ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኖቤል ሽልማት የሰጠው የኖቤል ሽልማት ኮሚቴ በገዛ ፈቃዱ ሥልጣኑን እንዲለቅ የጠየቁት በኖርዌይ ኦስሎ ቢዮርኬስ ዩኒቨርሲቲ የሰላምና የግጭት ጥናት ተመራማሪ የሆኑት ፕሮፌሰር ጄቲል ትሮንቮል ናቸው፡፡

የሰላምና የግጭት ጥናት አጭኚው ዘ ጋርዲያን ላይ ባስነበቡት መጣጥፍ በወቅቱ የኖቤል ሽልማትን የሰጡት ግለሰቦች በትግራይ ጦርነት አስነስተዋል ያሏቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩን በመቃወም የተከበረ ነው ያሉትን የኖቤል ኮሚቴነት ይልቀቁ ብለዋል፡፡

የኖቤል ኮሚቴ በወቅቱ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሽልማቱን ያበረከተው ከጎረቤት አገር ኤርትራ ጋር ሰላም እንዲሰፍን ላበረከቱት አስተዋጽኦ እንደነበር ያስታወሱት ትሮንቮል፣ አሁን ግን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ‹‹ሕግ ማስከበር›› በሚል ከኤርትራ እና ከአማራ ኃይሎች ጋር የጦር ወንጀል እንዲሁም በሰብአዊነት ላይ በሚፈጸም ወንጀል እንየተከሰሱ እንዲሚገኙ አንስተዋል፡፡

በኖርዌይ ኦስሎ ቢዮርኬስ ዩኒቨርሲቲ የሰላምና የግጭት ጥናት ተመራማሪ የሆኑት ፕሮፌሰር ጄቲል ትሮንቮል በተለይ በኢትዮጵያ፣ ኤርትራ እና ዛንዚባር በማተኮር ጥናታቸው የሚታወቁ ናቸው፡፡

እኚሁ አጥኚ ባለፈው ዓመት መጨረሻ በትግራይ ክልል ሕወሃት ምርጫ ባካሄደ ሰሞን በብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት ሰዎች ወደ አገራቸው እንደተባረሩ ቢነገርም፣ እርሳቸው ግን ኢትዮጵያ መቆየቴ ለደህንነትህ ጥሩ አይደለም ስለተባልኩ አገሩን ለቅቄያለሁ ብለው ነበር፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img