Thursday, October 10, 2024
spot_img

በሱዳን ደርፉር ግዛት በተቀሰቀሰ የጎሳ ግጭት የ36 ሰዎች ሕይወት አለፈ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ግንቦት 30፣ 2013 ― በሱዳን ደቡባዊ ዳርፉር ግዛት በተቀሰቀሰ ግጭት የ36 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 32 ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውንም ሲጂቲኤን አፍሪካ ዘግቧል።

ግጭቱ የተከሰተው በደቡባዊ ደርፉር በሚኖሩ ፌላታ እና ቴይሻ በተሰኙ ሁለት ጎሳዎች መካከል በተፈጠረ የመሬት ይገባኛል ግጭት እንደሆነ ዘገባው ጠቁሟል።

በሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት እና በአካባቢው በሚንቀሳቀሱ አማጺ ሀይሎች መካከል የተለያዩ ስምምነቶች ቢደረጉም በአካባቢው ጎሳን መሰረት ያደረጉ ገጭቶች በተደጋጋሚ እየተከሰቱ እንደሆነ ተገልጧል።

በአካባቢው ሰፍሮ የነበረው የመንግስታቱ ድርጅት እና የአፍሪካ ኅብረት የጋራ ሰላም አስከባሪ ኃይል ካሳለፍነው ጥር ጀምሮ በመውጣቱ የሱዳን ብሔራዊ ጦር አካባቢው ቢቆጣጠርም ግጭቶቹ ሊቆሙ አልቻሉም።

በዳርፉር እ.ኤ.አ 2003 በተከሰተ የጎሳ ግጭት 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ህዝብ የተፈናቀለ ሲሆን ካለፈው ዓመት ጀምሮ ደግሞ ግጭቶቹ በድጋሚ በማገርሸት ላይ እንደሚገኙ ዘገባው ጠቁሟል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img