Thursday, October 10, 2024
spot_img

አብን ‹‹አማራ ጨቋኝ ነው›› ከሚል ኃይል ጋር በምንም መንገድ ጥምር መንግሥት መመሥረትም ሆነ አብሮ መሥራት እንደማይፈልግ አስታወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ግንቦት 30፣ 2013 ― ፓርቲው ይህን ያለው በትላንትናው እለት በባህር ዳር ሙሉዓለም የባህል ማዕከል ባደረገው ሕዝባዊ ውይይት ነው፡፡

በዚሁ ውይይት ላይ ‹‹የኢትዮጵያን ሀገረ መንግስትነት የማይቀበሉ፣ በህዝቦች መካከል ጥርጣሬን የሚፈጥሩ እና የዘር ፍጅት ወንጀል ፈጽመዋል›› ካላቸው ኃይሎች ጋር እንደማይሰራም ፓርቲው ገልጿል።

አብን በቀጣዩ ምርጫ በተወሰኑ ቦታዎች ቢያሸነፍ ከገዢው ፓርቲ ጋር ጥምር መንግስት ይመሰርት እንደው ከአንድ ታዳሚ ለቀረበው ጥያቄ የአብን የፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ክርስቲያን ታደለ ምላሽ ሰጥተዋል። በዚህ ጉዳይ ላይ አብን የያዘውን ስትራቴጂክ አቋም ያብራሩት አቶ ክርስቲያን፤ ፓርቲያቸው ከምርጫው በፊት ሁለት ኃይሎች ነጥረው መውጣት አለባቸው ብሎ እንደሚያምን ገልጸዋል።

ይህን የፓርቲውን አቋም ያንጸባረቁት የአብን የፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ክርስቲያን ታደለ አብን በቀጣዩ ምርጫ በተወሰኑ ቦታዎች ቢያሸነፍ ከገዢው ፓርቲ ጋር ጥምር መንግስት ይመሰርት እንደሆነ ከአንድ ታዳሚ ለቀረበው ጥያቄ፣ ፓርቲያቸው ከምርጫው በፊት ሁለት ኃይሎች ነጥረው መውጣት አለባቸው ብሎ እንደሚያምን ገልጸዋል።

አቶ ክርስቲያን የመጀመሪያውን ኃይል ‹‹የዲሞክራሲ ካምፕ (ወገን)›› በሚል ያስቀመጡት ሲሆን፣ ሁለተኛውን ደግሞ ‹‹የጭቆና ኃይል›› ሲሉ ጠርተውታል። ‹‹እኛ በየትኛውም መመዘኛ ፍትህን፣ እኩልነትን፣ ነጻነትን እዚህ ላይ የሚያጠነጥን ፓርቲ ካለ ርዕዮት ዓለም ሳይገድበን በጋራ ለመስራት ሁሌም ዝግጁዎች ነን›› ማለታቸውን የዘገበው ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ነው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img