Sunday, October 6, 2024
spot_img

ኢድና ሞል በሐራጅ ሊሸጥ መሆኑ ተሰማ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ግንቦት 28፣ 2013 ― በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ አካባቢ የከተማዋ ልዩ የመዝናኛ አገልግሎት ስፍራ የሆነው ኢድና ሞል ከነሙሉ ሙሉ የመዝናኛ ቁሶቹ በሐራጅ ሊሸጥ መሆኑ ተሰምቷል፡፡

ኢድና ሞል የሚሸጠው ባለቤቱ የሆኑት አቶ ተክለብርሃን አምባዬ በሥማቸው በተቋቋመው የኮንስትራክሽን ድርጅት (ተክለብርሐን አምባዬ ኮንክትራክሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር) አማካኝነት ኢድና ሞልን በመያዣነት በመጠቀም ከባንክ የተበደሩትን ብድር ባለመመለሳቸው ብድሩን ያበደረው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የብድሩ መያዣ የሆነውን ኢድና ሞል በሐራጅ ለመሸጥ እንደተገደደ ሪፖርተር ዘግቧል፡፡

በዚህም ምክንያት ለንግድ አገልግሎት የሚለውን ሙሉ ሕንጻ፣ ሲኒማ ቤቶቹን እንዲሁም የሲኒማ ማሳያ መሳሪያዎችን እና ልዩ ልዩ የመዝናኛ /መጫወቻ ቁሶችን በሐራጅ ለመሸጥ የጨረታ ማስታወቂያ ሂደት ላይ ነው ተብሏል፡፡

በ1 ሺሕ 938 ካሬ ሜትር ስፋት የከተማዋ እምብርት ቦታ ላይ ያረፈውን ኢድና ሞል ከተጠቀሱት ተጨማሪ ንብረቶች ጋር በመነሻ ዋጋ 236 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር ለሐራጅ እንደሚቀርብም ዘገባው አመልክቷል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img