Thursday, October 10, 2024
spot_img

ኢዜማ ሙስና በሞት የሚያስቀጣ ወንጀል እንዲሆን አደርጋለሁ አለ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ግንቦት 28፣ 2013 ― የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) የሴቶች ጉዳይ ተጠሪ ካውሰር ኢድሪስ ‹‹ሙስና በሞት የሚያስቀጣ ወንጀል እንዲሆን እናደርጋለን፤ የሃይማኖት አባቶች እንዲያወግዙትም እንጠይቃለን›› ሲሉ በዛሬው እለት ተናግረዋል፡፡

ተጠሪዋ ይህን የተናገሩት ፓርቲው በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ከተማ ላይ ያለውን አቋም በተመለከተ ግልጽ ለማድረግ የሚያችል ሕዝባዊ ውይይት ‹‹የጋራ ህልም፤ የጋራ ከተማ›› በሚል መሪ ቃል ባካሄደበት ወቅት ነው፡፡

በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ለሀገር በሚጠቅሙ ጉዳዮች ላይ ከየትኞቹም ፓርቲዎች ጋር እንደሚሰራ አስታውቋል፡፡

በውይይት መድረኩ ‹‹ኢትዮጵያ የመኖር ያለመኖር ጥያቄ ውስጥ ናት›› ያሉት የፓርቲው መሪ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ፣ ‹‹ለሀገር በሚጠቅሙ ጉዳዮች ከአብንም፣ ከባልደራስም፣ ከብልጽግና ጋር እንሰራለን›› ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በመድተረኩ አዲስ አበባን በተመለከተም የተናገሩት ፕ/ር ብርሃኑ፣ በከተማዋ ላይ ካለው የልዩ ጥቅም ጥያቄ ጋር በተያያዘ ‹‹ለአንድ ዘር/ብሔር የሚሰጥ የተለየ ጥቅም የሚባል ነገር የለም›› ብለዋል፡፡

አዲስ አበባ ልትሰፋ እና ልታድግ እንደሚገባ የተናገሩም ሲሆን ‹‹በዙሪያዋ ያሉት አርሶ አደሮችም መጠቀም አለባቸው›› ብለዋል፡፡ ሲል የዘገበው አል ዓይን ሚዲያ ነው።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img