Thursday, October 10, 2024
spot_img

በደቡብ ክልል በጉራፈርዳ ወረዳ ስድስት የጸጥታ ኃይሎች በታጣቂዎች መገደላቸው ተሰማ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ግንቦት 28፣ 2013 ― ስድስት የደቡብ ክልል ልዩ ኃይል አባላት በቤንች ሸኮ ዞን በሚገኘው ጉራፈርዳ ወረዳ ውስጥ በትላንትናው ዕለት መገደላቸውን አንድ የአካባቢው ባለስልጣን ነግረውኛል ብሎ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል፡፡

የልዩ ኃይል አባላቱ የተገደሉት በወረዳው ስር ባለው ወጀምታ ቀበሌ እንደሆነም ነው የተነገረው፡፡

ጥቃት የተፈጸመባቸው የደቡብ ክልል ልዩ ኃይል አባላት፤ በወጀምታ ቀበሌ ልዩ ስሙ ሰንበሊጥ በተባለ ቦታ ባለ ካምፕ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ መሆናቸውን የጉራፈርዳ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ሲሳይ ሻሎም ተናግረዋል።

ስምንት የልዩ ኃይል አባላት፤ ትላንት አርብ ግንቦት 27 ከጠዋት ሁለት ሰዓት ገደማ፤ አንድ የካምፑን ሠራተኛ አጅበው ውሃ ለመቅዳት ወደ ወንዝ ሲሄዱ ተኩስ እንደተከፈተባቸው አስረድተዋል።

በጥቃቱ ስድስት የልዩ ኃይል አባላት ሲገደሉ አብሯቸው የነበረው የካምፑ ሰራተኛ ጉዳት ደርሶበት ሕክምና ላይ ይገኛል ብለዋል። ለአጀባ ከተሰማሩት የጸጥታ ኃይሎች ውስጥ ሁለቱ ምንም ጉዳት እንዳልደረሰባቸውም አክለዋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img