Tuesday, October 8, 2024
spot_img

ትራምፕ ከፌስቡክ እና ኢንስታግራም ለ2 ዓመት ታገዱ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ግንቦት 28፣ 2013 ― የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከፌስቡክ እና ከኢንስታግራም ለሁለት ዓመታት መታገዳቸውን የፌስቡክ ኩባንያ ዛሬ አስታውቋል፡፡

ፌስቡክ እገዳው መጀመሪያ ከተጣለበት ከፈረንጆቹ ጥር 7፣ 2021 አንስቶ ለሁለት ዓመት ተግባራዊ የሚሆን ነው ብሏል።

ኩባንያው ፕሮቶኮሎቹን በሚጥሱ ህዝብ በሚከተላቸው አካላት ላይ ‹‹ከፍተኛ ቅጣቶችን›› ተግባራዊ እያደረገ መሆኑን አክሏል። ግዙፉ የማኅበራዊ ትስስር መድረክ ፌስቡክ በጥር ወር የትራምፕን አካውንት ያገደው ነውጠኛ ደጋፊዎቻቸው ዋሺንግተን የሚገኘውን ካፒቶል ሒል ሕንጻን ካጠቁ በኋላ ነበር።

በወቅቱ የኩባንያው አለቃ ማርክ ዙከርበርግ ውሳኔውን በተመለከተ ሲናገር ‹‹ፕሬዝዳንቱ በዚህ ወቅት የእኛን አገልግሎት እንዲጠቀሙ መፍቀድ ያለው አደጋ ከፍተኛ መሆኑን እናውቃለን›› ብሎ ነበር።

የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በተመሳሳይ ከትዊተር እና ከዩትዩብም መታገዳቸው አይዘነጋም፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img