Thursday, October 10, 2024
spot_img

ኢዜማ አዲስ አበባን በተመለከተ በሚነሱ ጥያቄዎች ላይ ከነዋሪዎች ጋር ሊወያይ ነው

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ግንቦት 27፣ 2013 ― የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) የአዲስ አበባ ከተማን በተመለከተ በሚያራምዳቸው አቋሞች ላይ ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ የሚሰጥበት የውይይት መድረክ ማዘጋጀቱን አስታውቋል፡፡

ነገ ቅዳሜ ግንቦት 28 በአዲስ አበባው ዋቢ ሸበሌ ሆቴል በሚደረገው በዚሁ ውይይት ላይ የኢዜማ መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋን ጨምሮ ሌሎችም የፓርቲው ከፍተኛ ኃላፊዎች እንደሚገኙም ገልጿል።

የቅዳሜው የውይይት መድረክ ፓርቲው በሌሎች የአገሪቱ ከተሞች ካደረጋቸው ህዝባዊ ውይይቶች ጋር ‹‹በይዘት ተመሳሳይ›› መሆኑን የተናገሩት የኢዜማ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል የኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ ዘላለም ወርቅአገኘሁ፤ ዋና ዓላማው ‹‹አዲስ አበባን አስመልክቶ የሚነሱ ጥያቄዎችን ግልጽ ማድረግ ነው›› ብለዋል።

እስከ 500 የሚገመቱ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ይሳተፉበታል ተብሎ በሚጠበቀው በቅዳሜው ውይይት ላይ ያነጋግራሉ ተብለው ከሚጠበቁ ጉዳዮች መካከል አንዱ የቀበሌ ቤቶች ጉዳይ ነው። ይህ የፓርቲው ዕቅድ የከተማ ነዋሪዎችን ጨምሮ ብዙ ሰዎችን ግራ እንዳጋባ የኢዜማ የኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ ይቀበላሉ። ‹‹ቃል የገባናቸው ጉዳዮች ላይ የአፈጻጸም ጥያቄ ያላቸው ህዝቦች አሉ። እነሱ ላይ ማብራሪያ እንሰጣለን›› ሲሉ ነግረውኛል ብሎ የዘገበው ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ነው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img