Tuesday, October 8, 2024
spot_img

የምዕራቡ ዓለም በኢትዮጵያ ላይ ክብረ ነክ አቋም ማንጸባረቁን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቃል አቀባዩ ተናገሩ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ግንቦት 27፣ 2013 ― የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ቃል አቀባይ የሆኑት ቢልነኔ ሥዩም በአሁኑ ወቅት የምዕራቡ ዓለም በኢትዮጵያ ላይ ክብረ ነክ አቋም እያንጸባረቀ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

ቢልለኔ ይህን የተናገሩት የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በጥቅምት ወር የተቀሰቀሰውን የፌዴራል መንግሥት እና የሕወሃት ጦርነት በኋላ ለመጀመሪያ ገዜ በሰጠው መግለጫ ወቅት ነው፡፡

በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሕፈት ቤት ውስጥ በተካሄደው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ከቃል አቀባይዋ ቢልለኔ ሥዩም በተጨማሪ የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ በትግራይ ክልል ውስጥ ስለተከሰተውና አሁን ስላለው ሁኔታ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ሁለቱ የመንግሥት ባለሥልጣናት በክልሉ ስላለው የጸጥታ ሁኔታ፣ የእርዳታ አቅርቦት፣ ተፈጸሙ ስለተባሉ ሰብአዊ መብት ጥሰቶችና በመንግሥት በኩል እየተወሰዱ ስላሉ እርምጃዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በመንግሥት ላይ የሚቀርቡ ክሶችን በተመለከተም ቢልለኔ በክልሉ ‹‹ረሃብ እንደ ጦርነት መሣሪያ አየዋለ ነው የሚለው ክስ ተቀባይነት የለውም›› ሲሉም የዓለም አቀፍ ድርጅቶች እና የመብት ተሟጋቾችን ክስ አጣጥለዋል።

በሌላ በኩል በጤና ድጋፍ ረገድ 72 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር እንደተመደበና 12 አምቡላንስ መሠማራታቸውን ጠቅሰው፣ ‹‹የሕክምና አገልግሎት መስጫ ሙሉ በሙሉ ወድሟል የሚለው ትክክል አይደለም›› ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ቢልለኔ ሥዩም በመግለጫቸው ላይ እንደተናገሩት በበርካታ ወገኖች ከትግራይ ክልል እንዲወጡ ሲጠየቁ የነበሩት የኤርትራ ወታደሮች ከኢትዮጵያ ግዛት ‹‹መውጣት ጀምረዋል›› ብለዋል።

የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ ዶክተር ጌድዮን ጢሞቲዮስ በበኩላቸው በጋዜጣዊው መግለጫ ላይ በሕግ በኩል እየተወሰዱ ስላሉ እርምጃዎችና ተፈጸሙ ከተባሉ የመብት ጥሰቶች አንጻር ስለተደረጉ ምርመራዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ ‹‹ሕወሓት በአፋር፣ በአማራ፣ በቤንሻንጉል እና በኦሮሚያ ክልሎች የሚያስታጥቃቸው እና የሚደግፋቸው ኃይሎች የአገር ሰላም እያናጉ ነው›› ብለዋል።

በትግራይ ክልል ውስጥ ጦርነቱ በተቀሰቀሰበት ጊዜ በሰሜን ዕዝ ላይ ‹‹የተቀነባበረ ጥቃት ተፈጽሟል›› ያሉ ሲሆን፣ የኤሌክትሪክ እና የቴሌኮም መስመሮች በሕወሓት አመራር መቋረጣቸውን አስታውሰው፣ ‹‹ብዙዎቹ በወንጀል የሚጠረጠሩት ታስረዋል›› ሲሉ ጠቁመዋል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ሕገ መንግሥትን በመጣስ፣ በሽብርተኛነት እና በሌሎችም ወንጀሎች እንደሚጠየቁ በመግለጫቸው ላይ አመልክተዋል።

በወሲባዊ ጥቃት፣ ተዋጊ ባልሆኑ ሰዎች ያልተመጣጠነ ኃይል በመጠቀም የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባላት ላይ የቀረበውን ክስ በተመለከተም ምርመራ ተደርጎ እርምጃ እተወሰደ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ዶክተር ጌድዮን በዚህም መሠረት 28 ወታደሮች ክስ እንደተመሠረተባቸው እና በወሲባዊ ጥቃት የተጠረጠሩ 25 ወታደሮችም ላይም ክስ እንደተከፈተ ተናግረዋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img