Sunday, September 22, 2024
spot_img

የመንግሥታቱ ድርጅት የእርዳታ ማስተባበሪያ ቢሮ በትግራይ ያለው የጸጥታ ችግር አሁንም የሰብአዊ አቅርቦቱን እያስተጓጎለ መሆኑን አስታወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ግንቦት 26፣ 2013 ― የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ እርዳታ ማስተባበሪያ ቢሮ በትግራይ ክልል ያከለው የጸጥታ ሁኔታ አሁንም የእርዳታ አቅርቦቶችን እያስተጓጎለ መሆኑን በወጣው መግለጫ ላይ አስታውቋል፡፡

በክልል በተለይ ገጠራማ አካባቢዎች ግጭቶች እንደሚስተዋሉ ያመለከተው ቢሮው፣ በንጹሐን እና በረድኤት ሠራተኞች ላይ የሚደርሰው ጥቃትም ቀጥሏል ነው ያለው፡፡

ከምግብ ጋር በተያያዘም በክልሉ ሕፃናት ለተመጣጠነ የምግብ እጥረት ተጋላጭ መሆናቸውን በመግለጽ አሳሳቢ መሆኑን አንስቷል፡፡ በሌላ በኩል በክልሉ የጤና ተቋማት አሁንም ጾታዊ ጥቃት የደረሰባቸውን ሴቶች እና ከጥቃት የተረፉ ሰዎችን እያከሙ መሆናቸውን የመንግሥታቱ ድርጅት የእርዳታ ማስተባበሪያ ቢሮ ገልጧል፡፡

ቢሮው እስከ ግንቦት 23 ድረስ ባለው ጊዜ የተባበሩት መንግሥታት እና አጋሮቹ በክልሉ እርዳታ ከሚያስፈልጋቸው 5 ነጥብ 2 ሚሊዮን ሰዎች መካከል 2 ነጥብ 8 ሚሊዮን የሞሆኑትን መድረሱን ያመለከተ ሲሆን፣ አሁንም የሰብአዊ አቅርቦት ከነበረው ይበልጥ ከፍ ሊል እንደሚገባም አሳስቧል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img