Sunday, October 6, 2024
spot_img

የመገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የሃይማኖት ጣቢያዎችን ምዝገባ ማራዘሙን አስታወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ግንቦት 25፣ 2013 ― በ10 ቀን ውስጥ ይጀመራል ተብሎ የነበረው የሃይማኖት የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ምዝገባ በበይነ መረብ ሚዲያዎች ምዝገባ ሂደት መዘግየት ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስሥልጣን አሳውቋል።

የፊታችን ዐርብ ግንቦት 17፣ 2013 እንደሚጀመር ሲጠበቅ የነበረው ምዝገባ የአንድ ወር የጊዜ ገደብ ተይዞለት የነበረ ሲሆን፣ ባለሥልጣኑ የቴሌቭዥኖች የምዝገባ ሂደት ላይ ጣቢያዎቹ በቅድሚያ ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶችም ለመራዘሙ እንደ ተጨማሪ ምክንያት እንደሆነ ገልጧል፡፡

የባለሥልጣኑ ምክትል ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ዮናታን ተስፋዬ ለአዲስ ዘይቤ ድረ ገጽ እንደተናገሩት የሃይማኖት ቴሌቭዥኖች ለመመዝገብ የተለያዩ መስፈርቶችን ማሟላት አለባቸው፡፡ ከነዚህ መካከል መካከል የቴሌቪዥን ጣቢያው አስተምህሮቱን የሚያስተላልፍለት የሃይማኖት ተቋም በሰላም ሚኒስቴር የተመዘገበ መሆኑ፤ የሃይማኖት ተቋሙ ለጣቢያው የሚሰጠው የድጋፍ ደብዳቤ እና እንደማንኛውም የንግድ ድርጅት ከሚመለከተው የመንግሥት አካል የሚሰጥ ዕውቅና ማቅረብ ዋና ዋናዎቹ ናቸው።

‹‹እነዚህን መስፈርቶች ለማሟላት ጊዜ ስለሚያስፈልግ በዚህ ቀን ምዝገባው ያበቃል ማለት አይቻልም›› ሲሉ አቶ ዮናታን ተናግረዋል። በተያዘው ዓመት መጋቢት ወር በፌደራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ሥራ ላይ የዋለው አዲሱ የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ፤ የሃይማኖት ተቋማት የብሮድካስት አገልግሎት ፍቃድ እንዲያገኙ የሚደነግግ ነው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img