Thursday, October 10, 2024
spot_img

ኬሎ ሚዲያ የለቀቅኩት የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር ትክክለኛ ስለመሆኑ ጥርጥር የለኝም አለ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ግንቦት 25፣ 2013 ― ከትላንት በስትያ ግንቦት 23 ምሽት ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የባለፈው ሳምንት የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ስብሰባ ላይ ተናግረውታል በሚል የድምጽ ፋይል የለቀቀው ኬሎ ሚዲያ አሁንም ቢሆን ያሠራጨሁት ድምጽ ትክክለኛ ስለመሆኑ ጥርጥር የለኝም ብሏል፡፡

ሚዲያው ይህን ያለው የድምጹን መለቀቅ ተከትሎ መንግሥት ድምጹን ‹‹በውሸት የተቀነባበረና ጠ/ሚኒስትሩ በተለያያየ ግዜ የተናገሩትን በመቁረጥና በመቀጠል የተፈጠረ የሀሰት መረጃ መሆኑን እወቁት›› በማለቱና በማኅበራዊ ትስስር ገጾች ላይ የድምጹ ተአማኒነት ጥያቄ ውስጥ የሚያስገቡ የተለያዩ ማስረጃ ናቸው የተባለሉ የድምጽ እና የምስል ማስረጃዎች ወጥተው መነጋገሪያ ከሆነ በኋላ ነው፡፡

እንደ ኬሎ ሚዲያ ሥራ አስኪያጅ ኪያ ሰኚ ከሆነ በሚመሩት ሚዲያ የተለቀቀው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ድምጽ፣ በድምጽ ባለሞያዎች ትክክለኛ ስለመሆኑ የተረጋገጠ ሲሆን፣ ከዚህ በተጨማሪም ከሌላ የሚያምኑት ምንጭ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተለቀቀው ድምጽ ላይ አንጸባርቀውታል የተባለውን የንግግር ይዘት ስለመነሳቱ አረጋግጠዋል፡፡

ሥራ አስኪያጁ አክለውም በድምጹ ጉዳይ ማጣራት እፈልጋለሁ ለሚል ሦስተኛ አካል ዋናውን ቅጂ ለመስጠት ፍቃደኛ መሆናቸውንም ገልጸዋል፡፡

ኬሎ ሚዲያ በለቀቀውና መንግሥት ‹‹በውሸት የተቀነባበረ ነው›› ባለው ድምጽ ላይ ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ እስከሚቀጥለው 10 ዓመት ድረስ ማንም ሰው መንግሥት መሆን እንደማይችልና ሥልጣን ለማስረከብም ፈቃደኛ እንዳልሆኑ ሲናገሩ ይደመጣል፡፡

አክለውም «እሞታታለሁ እንጂ ስልጣን አልሰጥም» ሲሉም በድምጹ ላይ ተሰምተዋል። ለዚህም ብዙ እርምጃዎች እንደሚወሰዱ የገለጹት ጠ/ሚሩ፣ «ለዚህ የተዘጋጀው ግብረኃይልም ሥራውን ጀምሯል» ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img