Thursday, October 10, 2024
spot_img

የአማራ ክልል በጦርነት ሰበብ ያወጣሁትን 2 ቢሊዮን ብር የፌዴራል መንግሥት ያወራርድልኝ ማለቱ ተሰማ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ግንቦት 25፣ 2013 ― የአማራ ክልላዊ መንግሥት በትግራይ በነበረው ጦርነት ሰበብ ያወጣሁትን 2 ቢሊዮን ብር የፌዴራል መንግሥት ያወራርድልኝ ማለቱ ተሰምቷል፡፡

ክልሉ የጠየቀው የካሳ ገንዘብ ለቆሰሉ የአገር መከላከያ ሠራዊት ወታደሮች የሕክምና እርዳታ ያወጣው መሆኑን መጥቀሱን ፎርቹን ጋዜጣ አስነብቧል፡፡

የአማራ ክልል ይኸው ሒሳብ እንዲወራረድ የጠየቀበትን ደብዳቤ ለሰላም ሚኒስቴር ማስገባቱ የተነገረ ሲሆን፣ የደብዳቤውን ግልባጭ ለጤና ሚኒስቴር ማስገባቱንም ሚኒስቴር ዲኤታዋ አለምፀሐይ ጳውሎስ እንዳረጋገጡለት ጋዜጣው በዘገባው አመልክቷል፡፡

በጥቅምት የመጨረሻ ሳምንት የተቀሰቀሰው የፌዴራል መንግሥት እና የሕወሃት ኃይሎችን ጦርነት ተከትሎ በአጎራባቹ የአማራ ክልል የሚገኙ የጤና ተቋማት የእለት ተለት ሥራቸውን ለማከናወን ተቸግረው እንደነበር ተነግሯል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img