Wednesday, October 9, 2024
spot_img

የጠ/ሚሩ ነው የተባለው ድምጽ በቆርጦ መቀጠል የተፈጠረ የሐሰት መረጃ ነው ሲል የጠ/ሚር ጽሕፈት ቤት አስታወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ግንቦት 23፣ 2013 ― ባለፈው ሳምንት በብልጽግና ፓርቲ ስብሰባ ወቅት በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተባለ በማስመሰል የተለቀቀው የድምፅ ፋይል በውሸት የተቀነባበረና ጠ/ሚኒስትሩ በተለያያየ ግዜ የተናገሩትን በመቁረጥና በመቀጠል የተፈጠረ የሀሰት መረጃ መሆኑን እወቁት ሲል የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በፌስቡክ ገጹ ላይ ገልጧል፡፡

ጽሕፈት ቤቱ አክሎም ‹‹በዚህ የሀሰት መረጃ ዘመን እና ምርጫው እየተቃረበ ባለበት ወቅት ዜጎች አለመግባባትን ለመፍጠር ያተኮሩ እንደነዚህ ዓይነቶቹ የማሳሳት የመረጃ ዘመቻ ዓይነቶች እንዳይታለል›› ሲል አሳስቧል፡፡

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ባለፈው ሳምንት በተካሄደው የብልጽግና ፓርቲ የሥራ አስፈጻሚ ስብሰባ ማጠቃላያ ላይ ተናግረውታል ተብሎ ‹‹ኬሎ›› በተባለ የኦንላይን ሚዲያ በተለቀቀው የድምጽ ቅጂ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እስከሚቀጥለው 10 ዓመት ድረስ ማንም ሰው መንግሥት መሆን እንደማይችልና ሥልጣን ለማስረከብም ፈቃደኛ እንዳልሆኑ ሲናገሩ ይደመጣል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img