Monday, November 25, 2024
spot_img

ሰበር ዜና ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ለቀጣዮቹ 10 ዓመታት ሥልጣን ለማስረከብ ፈቃደኛ አለመሆናቸውን የሚናገሩበት በምሥጢር የተቀዳ ድምጽ ቅጂ ይፋ ሆነ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ግንቦት 23፣ 2013 ― ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ባለፈው ሳምንት በተካሄደው የብልጽግና ፓርቲ የሥራ አስፈጻሚ ስብሰባ ማጠቃላያ ላይ ተናግረውታል ተብሎ ‹‹ኬሎ›› በተባለ የኦንላይን ሚዲያ በተለቀቀ የድምጽ ቅጂ፤ እስከሚቀጥለው 10 ዓመት ድረስ ማንም ሰው መንግሥት መሆን እንደማይችልና ሥልጣን ለማስረከብም ፈቃደኛ እንዳልሆኑ ተናግረዋል፡፡

ምርጫው እንዳይራዘም ብልጸግና ፓርቲ ፍላጎት እንደነበረው የገለጹት ጠ/ሚ ዐቢይ የኮሮና ቫይረስ መምጣት ምርጫውን ለማራዘመ ፓርቲያቸውን እንዳስገደደው አስታውሰዋል። በዚሁ የድምጽ መልዕክት «እንደምታውቁት ፖለቲከኛ የሚባለው ኃይል አክቲቪስቱን ጨምሮ ሥልጣን ለመያዝ ነው የሚሠራው» ያሉ ሲሆን፣ የፓርቲያቸው ካድሬዎች በዚህ ሂደት ጥቃቅን ስህተቶችን ማረም መቻል እንዳለባቸውና አንድም ስህተት ቢሆን ብዙ ጉዳት ሊያደርስ እንደሚችል አስምረውበታል።

ጠ/ሚሩ «በዚህ ምርጫ ስልጣን ለመያዝ የሚፎካከሩ የፖለቲካ ሰዎች፥ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ሚዲያዎች ከሚገመተው በላይ ብዙ ኃይሎች ከቅርቡም ከሩቁም» መኖራቸውን በመናገር ይህ እንደሚያስፈራቸውም ገልጸዋል።

ነገር ግን «እስከሚቀጥለው 10 ዓመት ድረስ ማንም ሰው መንግሥት መሆን አይችልም» በሚል አቋማቸውን በግልጽ አስቀምጠዋል።

«እሞታታለሁ እንጂ ስልጣን አልሰጥም» ሲሉም በድምጹ ላይ ተሰምተዋል። ለዚህም ብዙ እርምጃዎች እንደሚወሰዱ የገለጹት ጠ/ሚሩ «ለዚህ የተዘጋጀው ግብረኃይልም ሥራውን ጀምሯል» ብለው ሲናገሩ ተደምጠዋል። መንግሥታቸው በሚወስደው እርምጃ ሰበብ «ከፍተኛ የሆነ ፍጅት፣ ደም መፋሰስ» ሊፈጠር እንደሚችል ያልሸሸጉት ጠ/ሚ ዐቢይ «ነገር ግን ከወዲሁ እርገጠኛ ሆኔ የምነግራችሁ ጥርጣሬም ምስጢርም የለውም፣ ምርጫውን ከወዲሁ አሸንፈናል፤ በቀላሉ ነው ያሸነፍነው።» ሲሉ ለፓርቲያቸው ሥራ አስፈጻሚ አባላት ተናግረዋል።

በተለቀቀው የሦስት ደቂቃ ድምጽ ማጠቃላያ ላይ ጠ/ሚሩ ስለ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ሲናገሩ የተሻለ እቅድ እንዳላቸው ያሳወቁ ሲሆን፣ «በተቻለ መጠን ምርጫውን አጨናግፈን፤ የሚፎካሩ ኃይሎች ተስፋ እንዲቆርጡ የማድረግ ትልቅ ኃላፊነት አለብን» እንዲሁም «ካለፍንባቸው ፈተናዎች አንጻር ይህን ማሳካት ከባድ አይደለም» ሲሉም ተደምጠዋል። ይህ ብቸኛውን መንገድ እንዲሳካና እንዳይበላሽም የፓርቲኣቸው አመራሮች «ድርብ ኃላፊነት ወስደው እንዲያሳኩት ጠይቀዋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img