Wednesday, October 9, 2024
spot_img

ጉራጊኛ ቋንቋ ተናጋሪ እያጣ በመምጣቱ የመጥፋት አደጋ ተጋርጦበታል ተባለ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ግንቦት 23፣ 2013 ― የጉራጌ ማኅበረሰብ ቋንቋ የሆነው ጉራጊኛ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተናጋሪ እያጣ መምጣቱን እና ይህንኑ ተከትሎም የመጥፋት አደጋ እንደተጋረጠበት ተነግሯል::

በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የኮምፒውቲንግ እና ኢኖፎርማቲክስ ኮሌጅ ዲን መምህር ኮራብዛ ሸዋረጋ ነግረውኛል ብሎ ብስራት ራድዮ እንደዘገበው 3 ሚልዮን ገደማ ይደርሳሉ ተብለው ከሚገመቱት የጉራጌ ማኅበረሰብ ተወላጆች ውስጥ ከ25 በመቶ የማይበልጡት ብቻ ናቸው ቋንቋውን አቀላጥፈው የሚናገሩት።

ከዚህ በተጨማሪም የጉራጊኛ ቋንቋ በብዛት በዕድሜ በገፉ ሰዎች ዘንድ ብቻ ተዘውትሮ የሚነገር ሆኖ መቅረቱ በአንፃሩ በጉልምስና እና በወጣትነት የዕድሜ ዘመናቸው ላይ የሚገኙ የብሄሩ ተወላጆች ከጉራጊኛ ይልቅ አማርኛ አብዝቶ የመናገር ዝንባሌ ውስጥ መግባታቸው ቋንቋው ተናጋሪ እያጣ እንዲሄድ ማድረጉን የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ መምህሩ አቶ ኮራብዛ ሸዋረጋ ገልጸዋል።

ለመፍትሄው ‘የጉራግኛ ቋንቋን ከተናጋሪ ዕጦት እታደገዋለሁ’ የሚለዉ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ፣ ቋንቋውን በመጀመሪያ ዲግሪ እና በሌሎች አጫጭር ሥልጠናዎች ለማስተማር ሥርዓተ ትምህርት የመቅረፅ እና የትምህርት ክፍል የማደራጀት ስራ በማከናወን ላይ ነው ተብሏል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img