Wednesday, October 9, 2024
spot_img

የስፖርታዊ ማቋመሪያ (ቤቲንግ) ፍቃድ መሰጠት ቆመ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ግንቦት 23፣ 2013 ― የስፖርታዊ ማቋመሪያ (ቤቲንግ) ፍቃድ ለጊዜዉ መስጠት ማቆሙን የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር አስታውቋል፡፡

የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተሩ አቶ ቴዎድሮስ ነዋይ እንደገለጹት የእግር ኳስ ቤቲንግ (ቁማር) ከ2012 ግንቦት ጀምሮ መስፋፋቱን እና በርካታ ሰዎች ወደ ውርርዱ እንዳዘነበሉ የተናገሩት ዳይሬክተሩ፣ የተለያዩ ስፖርታዊ ውድድሮች ላይ በተለይም የእግር ኳስ ላይ በውርርድ ገንዘብ በማስያዝ የሚካሄድ ቁማር መሆኑን ተናግረዋል።

ከዚህም ጋር ተያይዞ ከኅብረተሰቡ ቅሬታዎች እና ትችቶች በሰፊው እየቀረቡ መምጣታቸውን ተናግረዋል።

በመሆኑም አስተዳደሩ ችግሩን ለመፍታት የተለያዩ ጥናቶች አካሂዶ የስፖርታዊ ውርርድ መመሪያዎች ላይ ማሻሻያ አስኪያደርግ ድረስ ለጊዜዉ የቤቲንግ ፈቃድ እንደማይሰጥ ገልጿል። ከስፖርታዊ ውርርዱ ጋር ተያይዞ ኅብረተሰቡ ለአስተዳደሩ እንደ ችግር ካቀረባቸዉ ውስጥ፣ ወጣቱ ወደ ጨዋታው በስፋት መሰማራቱ፣ ተማሪዎች ጊዜያቸዉን በቤቲንግ ማጥፋታቸው፣ የገንዘብ አያያዝ ሥርዐቱ ትክክል አለመሆን እና በአንዳንድ ቦታዎችም የሕገ ወጥ የቤቲንግ መጫወቻ ቤቶች መከፈትን ይጠቀሳሉ። በተጨማሪም ኅብረተሰቡ የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ቁጥጥር ማነሱን ጨምሮ የተለያዩ በርካታ ቅሬታዎችን አንስቷል።

በ2012 የቤቲንግ ፍቃድ የተሰጣቸዉ 42 ደርጅቶች መሆናቸውን አስታዉሰዉ፣ ዘንድሮም ፈቃድ የጠየቁ በርካታ እንደነበሩ ዳይሬክተሩ ተናግረዋል። የቁማር ጨዋታዉ ጥንቃቄ እና ትኩረት ሊሰጠዉ የሚገባ ጉዳይ በመሆኑ መጀመሪያ ብሔራዊ ሎተሪ ማሻሻያዎችንና ችግሮችን መቅረፍ እንዳለበት አመላክቷል።

ከብሔራዊ ሎተሪ ፍቃድ ወስደዉ በሥራዉ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ የአቋማሪ ድርጅቶች በበኩላቸዉ ቁጥጥር እንዳለና እድሜያቸዉ ከ18 አመት በታች የሆኑ ልጆች እንዳይገቡ ማስታወቂያ መለጠፋቸውን አታውቀዋል። ወደ ስፖርታዊ ውርርዱ ለመጫዎት የሚመጡ ራሳቸዉን የሚያውቁና አስበዉበት የሚያደርጉት ነገር በመሆኑ ለችግር እንዴት ሊጋለጡ ይችላሉ ብለዋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img