Monday, October 7, 2024
spot_img

ዛምቢያ ለዕድሜ ልክ እስረኞች የሁለት ሳምንት ዕረፍት ፈቀደች

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ግንቦት 21፣ 2013 ― በዛምቢያ የዕድሜ ልክ እስረኞች ተገምግመው ‹‹ጥሩ ሥነ ምግባር›› ካሳዩ ቤተሰቦቻቸውን ለመጎብኘት የሁለት ሳምንት ዕረፍት ማግኘት ይጀምራሉ ተብሏል፡፡

በአገሪቱ ፕሬዚዳንት ኤድጋር ሉንጉ በተፈረመው አዲስ ሕግ መሠረት ኅብረተሰቡ ላይ አደጋ አይፈጥሩም ተብለው የተመረጡት እስረኞች ፈቃድ ይሰጣቸዋል፡፡

እንደ ዛምቢያ ኮሚሽነር ጄነራል ቺሴላ ቼሌሼ ከሆነ መጸጸታቸውን የሚያሳዩ እና ከወንጀል የራቁ እስረኞች በአዲሱ ሕግ ይጠቀማሉ።

ፍርደኞቹ እነዚህ መብቶችን የሚያገኙት የዛምቢያ ማረሚያ አገልግሎት ለፕሬዝዳንት ሉንጉ በጽሑፍ ካሳወቃቸው ብቻ ነው የተባ ሲሆን፣ ‹‹ወንጀል ከፈጸሙ ግን ፈቃዳቸው ይሰረዛል›› መባሉንም ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

አያይዘውም ‹‹ኮሚሽን ጄኔራሉ እስረኞች የግል ወይም የቤተሰብ ጉዳዮችን እንዲታደሙ ፈቃድ የመስጠት መብት ያለው ሲሆን፤ ጊዜው በተለያዩ ሁኔታዎች በጄኔራል ኮሚሽነር ጽሕፈት ቤት የሚወሰን እና የሚሰጥ ነው›› ሲሉ አክለዋል።

አንዳንድ የዛምቢያ ዜጎች በትዊተር ገጻቸው አዲሱን ሕግ ለወንጀለኞች ‹‹የፌሽታ ቀን›› ሲሉ ሰይመውታል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img