Wednesday, October 9, 2024
spot_img

‹‹ድምጻችን ለነጻነታችን›› በሚል በመላው ሀገሪቱ ሰላማዊ ሠልፍ ሊካሄድ ነው

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ግንቦት 21፣ 2013 ― ‹‹ድምጻችን ለነጻነታችን›› በሚል መሪ ቃል በመላው አገሪቱ ወጣቶችን ያሳተፈ ሰልፍ ነገ እንደሚካሄድ ተገለጸ፡፡

ሰልፉ የውጭ አገራት በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ላይ የሚያደርጉትን ጣልቃ ገብነትና የሚያሳድሩትን ጫና በመቃወም የሚከናወን ነው ተብሏል።

የአሜሪካ መንግሥት ከሰሞኑ የጣለው የጉዞ ማዕቀብና በኢትዮጵያ ላይ የሚያሳድረው ጫና ሀገሪቱ ከድኽነት እንዳትላቀቅ ለማድረግ ከመፈለግ የመነጨ በመሆኑ በተለይም ወጣቶች ለአገር እድገት የበኩሉን በመወጣት የውጭ ጫናን መቃወም ይገባቸዋል ተብሏል። ይህ ወቅት ሕዝቡ ይበልጥ አንድነቱን ሊያጠናክርበት እንጂ ህብረ ብሔራዊነቱን ሊያደበዝዝ እንደማይገባ ተገልጿል።

ከምዕራባውያን ጫና ለመላቀቅ መስራት በትልልቅ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች ላይ ማተኮር እንደሚገባም ነው የተገለፀው።

መርሐግብሩ ነገ እሑድ ግንቦት 22 በተመሳሳይ ሰአት በመላ ሀገሪቱ የሚከናወን ሲሆን፣ በርካታ ቁጥር ያላቸው ወጣቶች እንደሚሳተፉ መገለጹን የዘገበው ኢቢሲ ነው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img