Wednesday, October 9, 2024
spot_img

በትግራይ ማዳበርያ እና ምርጥ ዘር ማከፋፈል መጀመሩን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ግንቦት 20፣ 2013 ― በትግራይ ክልል የማዳበርያና ምርጥ ዘር ማከፋፈል ተግባራት መጀመራቸውን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የግብርና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር አባዲ ግርማይ ገልጸዋል፡፡

ዶ/ር አባዲ በክልሉ 800 ሺሕ ኩንታል ማዳበርያ ለማስገባት መታቀዱን ገልጸው፣ እስካሁን 222 ሺሕ ኩንታል ማዳበርያ ከእጃችን ገብቷል ሲሉ እንደነገሩት አል ዐይን አማርኛ ዘግቧል፡፡

ምርጥ ዘርን በተመለከተ ከለጋሽ ድርጅቶች ድጋፍ ለማሰባበስብ እቅድ ተይዞ ነበር ያሉት ኃላፊው፣ የዘገየ ቢሆንም ከታቀደው 97 ሺሕ ኩንታል 38 ሺሕ ኩንታል ወደ ትግራይ ክልል መግባቱንም አክለዋል፤ እስካሁን 70 በመቶ የሚሆነው ማዳበርያና ምርጥ ዘር ወደ አርሶ አደሩ ለማዳረስ መቻሉን በመጠቆም፡፡

የቢሮ ኃላፊው የግብርና ግብአቶችን ለማዳረስ ጥረት እየተደረገ ቢሆንም ‹‹የትራንስፖርት ችግር›› ፈተና ሆኗልም ብለዋል፡፡

እኚሁ ኃላፊ በተመሳሳይ ከትላንት በስቲያ ረቡዕ ግንቦት 18 ለኢቢሲ ትግርኛ በሰጡት መረጃ ‹‹በዚህ ሳምንት ትራንስፖርት አግኝተናል፤ ዘር የምናጓጉዝ ይሆናል፤ ግን አሁንም ቢሆን የትራንስፖርት ችግር እጅግ ፈታኝ ነው›› ብለው ነበር፡፡

በስልክ ቆይታቸው ‹‹የማረስ ችግር ሁለተኛው ፈተና ነው›› ያሉት ዶ/ር አባዲ፤ በሚፈለገው ልክ ለማረስ ባይቻልም አርሶ አደሩ ባለው ለማረስ እየሰራ እንደሚገኝ አመልክተዋል፡፡

የቢሮ ኃላፊው ከአሁን ቀደም በሰጡት መረጃ የትግራይ ሕዝብ ‹‹ቤት ንብረቱ ተዘርፏል›› ማለታቸውን እንዲሁም፣ የእርሻ በሬዎች እንደሌሉት መናገራቸውን አል ዓይን አስታውሷል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img