Wednesday, October 9, 2024
spot_img

በአዲስ አበባ የኮቪድ መከላከያዎችን ተግባራዊ ያላደረጉ ከ160 ሺሕ በላይ ሰዎች በፖሊስ ተይዘዋል ተባለ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ግንቦት 20፣ 2013 ― በአዲስ አበባ ከተማ ከመስከረም ወር የመጨረሻ ቀናት አንስቶ የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከል እና ለቆጣጠር የወጣውን መመርያ ተላልፈዋል የተባሉ 167 ሺሕ 396 ግለሰቦች በፖሊስ መያዛቸው ተነግሯል፡፡

ግለሰቦቹ በፖሊስ የተያዙት በርካታ በመመርያው የኮቪድ 19 ቫይረስ ስርጭት መከላከያ የሆኑትን የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል (ማስክ) ሳያደርጉ መቀንሳቀስ እና አካላዊ ርቀትን ባለመጠበቅ መሆኑን ዋዜማ ራድዮ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር ፋሲካ ፋንታ ነግረውኛል ብሎ ዘግቧል፡፡

ከመጋቢት 17 እስከ ግንቦት 2፣ 2013 ባለው ጊዜ ብቻ በፖሊስ የያዙት እነዚህ 167 ሺሕ 396 ግለሰቦች ትምህርት ተሰጥቷቸው እና የማስጠንቀቂያ እርምጃ ብቻ ተወስዶባቸው ተለቀዋል፡፡

ኮማንደር ፋሲካ ይህ እርምጃ ብቻ የተወሰደው ‹‹ይሄን ሁሉ ሰው በየጊዜው እንሰር ብንል በቂ የማሰሪያ ስፍራ ካለመኖሩ በተጨማሪ ያን ሁሉ ሰው በአንድ ቦታ ማድረግ ጭራሽ ለበሽታው መስፋፋት ምክንያት መሆን ነው፡፡ ስለዚህ ያለው አማራጭ ማስተማሪያ የሆኑ ቅጣቶችን መቅጣት ነው፡፡›› ብለዋል፡፡

እንዲህ ያለው ማስተማሪያ ቅጣት ሲተገበር ለምን ብለው ውዝግብ በፈጠሩ 68 ግለሰቦች እና የቫይረሱን መከላከያ መንገዶች ፍፁም ችላ ባሉ 26 ተቋማት ላይ ምርመራ ተደርጎባቸው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

የጤና ሚኒስቴር ትናንት ግንቦት 19 ቀን 2013 ዓም ባወጣው መረጃ መሰረት አሁን ላይ በመላ ሀገሪቱ 270 ሺሕ 527 ግለሰቦች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን፣ 4 ሺሕ 127 ግለሰቦች ሕይወታቸው አልፏል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img