Wednesday, October 9, 2024
spot_img

ምርጫ ቦርድ ለሁለት የምርጫ ታዛቢዎች እውቅና ሰጠ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ግንቦት 19፣ 2013 ― የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በመንግስት ግብዣ መሰረት 6ተኛው አገር አቀፍ ምርጫ በጋራ ለመታዘብ በጋራ ለሚሰሩት ለዓለም አቀፍ ሪፕብሊካን ኢንስቲቲዩት (IRI) ለአለም አቀፍ ዴሞክራቲክ ኢንስቲቲዮት (NDI) የምርጫ መታዘብ እውቅናን ሰጥቻለሁ ብሏል።

ቦርዱ የድርጅቶቹ የጋራ የታዛቢ ቡድን ያቀረበውን የጥናት ዘዴ በማየት እንዲሁም በአለም አቀፍ ታዛቢዎች መሰረታዊ መርህዎችን እና የታዛቢዎች አለም አቀፍ የስነ ምግባር ደንብ በተከተለ መልኩ እንደሚሰሩ ስምምነት ላይ በመድረስ የመታዘብ እውቅናውን ሰጥቻለሁ ያለ ሲሆን፣ በአለም አቀፉ የኮቪድ ወረርሽኝ የተነሳ የታዛቢ ቡድኑ የሚያከናውነው የመታዘብ ተግባር የስፋት ውስንነት እንደሚኖረውና ይህንንም በሚያደርጋቸው ስራዎች እና ማጠቃለያዎች ላይ የሚገለጽ መሆኑን ታዛቢ ቡድኑ እና ቦርዱ በጋራ መግባባት ላይ እንደደረሱም ገልጿል።

ቦርዱ ከዚህ በፊት ለ45 የአገር ውስጥ የምርጫ ታዛቢዎች እውቅና መስጠቱንም አስታውሷል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img