Monday, October 7, 2024
spot_img

የአሜሪካው የሎቢ ድርጅት በትግራይ ጉዳይ እቅዴን አሳክቻለሁ አለ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ግንቦት 19፣ 2013 ― መቀመጫውን በአሜሪካ አሌክሳንድሪያ ባደረገው ትግራይ ሴንተር ፎር ኢንፎርሜሽን ኤንድ ኮሚኒኬሽን እንደተቀጠረ የሚነገረው ቮን ባተን ሞንትግዩ ዮርክ የተሰኘው የሎቢ ድርጅት በትግራይ ጉዳይ ያቀድኩት ግቡን መቷል ሲል በትዊተር ገጹ ላይ አስፍሯል፡፡

በትግራይ ተካሄዷል የሚባለውን ሰቆቃ ለማስተጋባት እንዲሁም የአሜሪካ ሴኔት ውሳኔ አሳልፎ በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ማዕቀብ እንዲጣል ሲሠራ መቆየቱን ያስታወሰው ድርጅቱ፣ ሁሉም ያቀድኳቸው ጉዳዮች ተሳክተውልኛል ብሏል፡፡

የሎቢ ሥራው በስኬት መጠናቀቁን ያመለከተው ድርጀቱ፣ ትግራይን ወክሎ ድምጽ ማሰማቱን እንደሚቀጥል አስታውቋል፡፡ ይኸው ድርጅት በትግራይ ጉዳይ የሎቢ ሥራን ማጠናቀቁን ተከትሎ በሕወሃት ደጋፊነት የሚታወቁ አክቲቪቶች የድርጅቱ ውል መራዘሙ ግድ መሆኑን በማኅበራዊ ሚዲያ ሲያስተጋቡ ታይተዋል፡፡

በትግራይ ክልል በጥቅምት ወር የመጨረሻ ቀናት የተቀሰቀሰውን የፌዴራል መንግሥት ጦርነት ተከትሎ የጦርነቱ ተፋላሚዎች የሆኑት ሕወሃት እና የፌዴራል መንግሥት የሎቢ ድርጅቶችን መቅጠራቸው ሲነገር ሰንብቷል፡፡

የፌዴራል መንግሥት አሜሪካ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲው በኩል ቬናብል የተሰኘ በወር 35 ሺሕ ዶላር የሚያስከፍል የሎቢ ድርጅት መቅጠሩ ይነገራል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img