Tuesday, December 3, 2024
spot_img

በትግራይ ክልል ከተሞች እየተካሄደ የሚገኘው ‹‹ጾመ ትግራይ›› መርሐ ግብር በዛሬው እለት ይጠናቀቃል ተባለ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ግንቦት 19፣ 2013 ― በትግራይ ክልል ጾመ ትግራይ በሚል የሚደረገው የጾም እና የጸሎት መርሐ ግብር በዛሬው እለት ይጠናቃል ተብሏል፡፡

ከትላንት በስትያ ግንቦት 17፣ 2013 በጀመረውና በክልሉ ላይ እየደረሰ ያለው ሰቆቃ እንዲቆምና ሰላም እንዲወርድ በሚል እየተካሄደ ባለው የጾም እና የጸሎት መርሐ ግብር በተለይ በመቀሌ፣ በአዲግራት እና በሽ እንዳሥላሴ የንግድ ተቋትማና የመጓጓዣ አገልግሎቶች እንደተቋረጡ ቪኦኤ ዘግቧል፡፡

ሆኖም በአንዳንድ አካባቢዎች የሥራ እንቅስቃሴ አቁማችኋል ተብለው የታሸጉ ሱቆች መኖራቸውም ተነግሯል፡፡

ዛሬ ይጠናቀቃል ተብሎ በሚጠበቀው የጾም እና የጸሎት መርሐ ግብር፣ በተለይ ሽረ እንደሥላሴ ከሌሎች አካባቢዎች ተፈናቅለው በዚያ የሚገኙ ተፈናቃዮችም መርሐ ግብሩን ተቀላቅለዋል ነው የተባለው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img