Sunday, November 24, 2024
spot_img

የግብጹ ፕሬዝዳንት ዐብዱልፈታህ አል ሲሲ ወደ ጅቡቲ አቀኑ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ግንቦት 19፣ 2013 ― የግብጹ ፕሬዝዳንት ዐብዱልፈታህ አል ሲሲ ከጂቡቲ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት እስማኤል ዑመር ጌሌ ጋር ለመወያየት በዛሬው እለት ወደ ጅቡቲ አቅንተዋል፡፡

የሁለቱ ሀገራት መሪዎች በጋራ ትብብር እና ተያያዥ ጉዳዮች በተለይም በፀጥታ፣ በወታደራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች የሁለቱን ሀገራት ትብብር ማጠናከር ዙሪያ እንደሚወያዩ የፕሬዝደንት አል ሲሲ ቃል አቀባይ ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም የግብፅና የጅቡቲ መሪዎች የጋራ በሆኑ ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ለመወያየት እና ሐሳቦችን ለመለዋወጥም አቅደዋል ነው የተባለው፡፡ በሌላ በኩል ግብጽ እና ኬንያ ወታደራዊ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

በናይሮቢ የተፈረመው ስምምነት ዓላማ የሁለቱን ሀገራት የጋራ ጥቅም ለማስጠበቅ የሚደረገው የሁለትዮሽ ትብብር አካል ነው ተብሏል፡፡

ግብፅ ከኬንያ ጋር ያደረገችው ወታደራዊ ስምምነት በተያዘው ዓመት በምሥራቅ አፍሪካ ከሚገኙ ሀገራት ጋር ያደረገችው አራተኛ ስምምነት ሲሆን፣ ከዚህ ቀደም ከሱዳን፣ ከኡጋንዳ እን ከብሩንዲ ጋር ወታደራዊ ስምምነት ፈርማለች፡፡

በተያያዘ ዜና ግብፅ እና ሱዳን በትናንትናው ዕለት ለ 6 ቀናት የሚቆይ ሁለገብ የጋራ ወታደራዊ ልምምድ በሱዳን ጀምረዋል፡፡ ኢትዮጵያ በሕዳሴው ግድብ ጉዳይ ከሁለቱ ሀገራት ጋር ውጥረት ውስጥ በምትገኝበት ወቅት የሚካሔደው ይህ ልምምድ፣ የናይል ጠባቂዎች (ናይል ፕሮቴክተርስ) የሚል ሥያሜ እንደተሰጠው አል ዓይን ዘግቧል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img