አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ግንቦት 18፣ 2013 ― የአሜሪካዋ ኦክላሆማ ግዛት ሴናተር ጂም ኢንሆፍ የባይደን አስተዳደር በኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ላይ የጣለውን የቪዛ ክልከላ ተቃውመዋል፡፡
ሴናተሩ ኢትዮጵያ የአሜሪካ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋት በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት መልእክት ላይ አስፍረዋል፡፡
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር ከጥቂት ቀናት በፊት በኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ላይ የቪዛ ክልከላ የሚጥል ውሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል፡፡