Friday, November 22, 2024
spot_img

ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ የቴሌኮም ድርሻ የመያዝ ፍላጎት እንደሌለው አስታወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ግንቦት 18፣ 2013 ― ባሳለፍነው ቅዳሜ ግሎባል ፓርትነርሺፕ ፎር ኢትዮጵያ በሚል ጥምረት በኢትዮጵያ ቴሌኮም ገበያ ለመሠማራት ጨረታ ካሸነፉት መካከል የሆነው ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ የቴሌኮም ድርሻ የመያዝ ፍላጎት እንደሌለው አስታውቋል፡፡

የኬንያው ስታር ጋዜጣ እንደዘገበው የኩባንያው ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት ፒተር ንዴግዋ በሰጡት መግለጫ ላይ በኢትዮጵያ ገበያ የቴሌኮም አገልግሎት ለመስጠት ካሸነፉት መካከል የሆነው የሚመሩት ኩባንያ የኢትዮጵያን የቴሌኮም ድርሻ ለመያዝ ከማቀድ ይልቅ፣ አሁን ባሸነፈበት አገልግሎት መስጠት ብቁ ተወዳዳሪ ለመሆን እንደሚሠሩ ገልጸዋል፡፡

ኩባንያው ወደ ኢትዮጵያ ለመግባት ፍላጎቱን በገለጸበት ጥቅምት 2019 በኃላፊዎቹ በኩል የቴሌኮም ድርሻ በመግዛት አሊያም ፍቃድ በመውሰድ ወደ ኢትዮጵያ ገበያ የመግባት አላማ እንደነበራቸው መናገራቸውን ዘገባው አስታውሷል፡፡

ይህንኑ አላማውን ፍቃድ በማግኘት ያሳካው ድርጅቱ፣ በጥምረት የብሪታንያው ቮዳፎን እና የደቡብ አፍሪካው ቮዳኮም አብረውት ይገኛሉ፡፡

በሌላ በኩል መንግሥት ሁለት የቴሌኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ፈቃድ ለመስጠት ባወጣው ጨረታ ለመወዳደር ፍላጎት የነበረው ግዙፉ የፈረንሣይ ኩባንያ ኦሬንጅ የኢትዮ ቴሌኮምን 40 በመቶ ድርሻ ለመሸጥ በሚወጣው ጨረታ ለመሳተፍ በመፈለጉ በመጨረሻው ሰዓት በጨረታው ላለመሳተፍ መወሰኑ ተነግሯል፡፡

መንግሥት ባወጣው ሁለት የቴሌኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ፈቃድ ጨረታ ለመሳተፍ ፍላጎታቸውን ከገለጹ 12 ዓለም አቀፍ የቴሌኮም ኩባንያዎች መካከል አንዱ የሆነው የፈረንሣዩ ኩባንያ፣ ለውድድር ከቀረቡት ሁለቱ ኩባንያዎች በተሻለ ሁኔታ ዓመታዊ የገቢ መጠንና ልምድ ቢኖረውም የኢትዮ ቴሌኮም የ40 በመቶ ድርሻ ለሽያጭ ሲቀርብ ለመሳተፍ በመምረጥ ለአዲሶቹ የቴሌኮም ፈቃድ ጨረታ ከመሳተፍ መቆጠቡን የገለጹ የኢትዮጵያ ቴሌኮሙዩኒኬሽን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ባልቻ ሬባ ናቸው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img