Wednesday, October 9, 2024
spot_img

ምርጫ ቦርድ እነ እስክንድር ነጋን በዕጩነት ለመመዝገብ እቸገራለሁ አለ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ግንቦት 18፣ 2013 ― የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ለምርጫ እንዲመዘገቡ የተወሰነላቸውን የባልደራስ ሊቀመንበር አቶ እስክንድር ነጋን ጨምሮ ሌሎችንም የፓርቲውን አባላት ለምርጫው ለመመዝገብ እደሚቸገር አስታውቋል፡፡

ቦርዱ ይህን ያለው ባልደራስ ውሳኔውን ተከትሎ በጻፈው ደብዳቤ እነ አቶ እስክንድር ነጋ በምርጫው በዕጩነት እንዲመዘገቡ ለጠየቀበት ደብዳቤ በሰጠው ምላሽ ነው፡፡

ምርጫ ቦርድ ምዝገባውን መፈጸም እቸገራለሁ ለማለቱ በምክንያትነት የዕጩ ምዝገባው የካቲት 30፣ 2013 መጠናቀቁን፣ እንዲሁም እያንዳንዱ እጩ ተወዳዳሪ በድምጽ መስጫ ወረቀት ላይ የሚኖረው ሥፍራ የሚወስን እጣ በመውጣቱና በዚሁ መሠረት የድምጽ መስጫ ወረቀቶች ሕትመት ተጠናቆ ወደ ምርጫ ጣቢያዎች የመላኩ ተግባር በቅርብ ጊዜ የሚጀመር መሆኑን አስቀምጧል፡፡

ይህን ተከትሎም የባልደራስ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት አስቸኳይ ስብሰባ መጥራታቸውን ፓርቲ በፌስቡክ ገጹ ላይ አስታውቋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img