Wednesday, October 9, 2024
spot_img

ኤርትራ በአሜሪካ የተጣለውን የቪዛ እገዳ ለቀጠናው የማይበጅ ነው አለች

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ግንቦት 18፣ 2013 ― ኤርትራ በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ከተከሰተው ቀውስ ጋር በተገናኘ በባለሥልጣኖቿ ላይ የቪዛ እቀባ መደረጉን ያልተገባ ውሳኔ ነው ብላዋለች፡፡

አገሪቱ በውጭ ጉዳይ ሚኒሰቴር መስርያ ቤት በኩል ባወጣቸው መግለጫ፣ ማዕቀቡ 30ኛ ዓመት የነጻነት በዓሏን በምታከብርበት ዋዜማ መሆኑ እጅጉን እንዳስቆጣት የገለጸች ሲሆን፣ ‹‹ምንም ማረጋገጫ የሌለው››ና ያልተገባ መሆኑንም ነው ያመለከተችው፡፡

የተጣለውን እገዳ በሚመለከትም ‹‹ለቀጠናው ሰላምና ፀጥታ እንዲሁም ህጋዊነት የሚበጅ አይደለም›› ብላለች፡፡

አገሪቱ አሁን በትግራይ የተፈጠረው ቀውስ ‹‹አሁን ላይ የፈረሰው ሕወሓት ጥቅምት 24፣ 2013 የወሰደውን ወታደራዊ እርምጃ ተከትሎ የተፈጠረ ነው›› መሆኑንም አመልክታለች፡፡

የህወሓት ወታደራዊ እቅድ ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን ኤርትራንም የሚጨምር እንደነበር ያመለከተው የውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ፣ ግጭቱ መጀመሩን ተከትሎ የህወሓት ኃይሎች ወደ ኤርትራ ሮኬቶችን ማስወንጨፋቸውን አስታውሷል፡፡

ከሰሞኑ በአሜሪካ መንግሥት በባለሥልጣናቱ ላይ የቪዛ እቀባ የተጣለባት ኤርትራ በጥቅምት ወር የተቀሰቀሰውን የሕወሃት እና የፌዴራል መንግሥት ጦርነት ተከትሎ ወታደሮቿ ወደ ኢትዮጵያ መሬት ዘልቀው በንጹሐን ላይ ግድያዎችንና የተለያዩ ግፎችን ማድረሳቸው ሲነገር ሰንብቷል፡፡

ጠቅላይ ሚኒሰትር ዐቢይ አሕመድ እና የኤርትራ ባለስልጣናት የኤርትራ ሰራዊት ከትግራይ ምድር ለቆ እንዲወጣ ተስማምተናል ቢሉም፤ እስካሁን የመውጣት ዝንባሌዎች እንደሌሉ የተለያዩ ዘገባዎች እያመለከቱ ይገኛሉ፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img