Wednesday, October 9, 2024
spot_img

በቤንች ሸኮ ዞን የጉራፈርዳ ወረዳ ነዋሪዎች በጸጥታ ስጋት አካባቢያቸውን ጥለው እየተሰደዱ እንደሆነ ተነገረ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ግንቦት 17፣ 2013 ― በቤንች ሸኮ ዞን በተለይም በጉራፈርዳ ወረዳ በሚገኙ ነዋሪዎች ላይ ታጣቂዎቹ ተደጋጋሚ ጥቃቶችን እየፈጸሙ በመሆኑ ቁጥራቸው ያልተገለጸ ሰዎች አካባቢያቸውን ጥለው በመሸሽ ላይ እንደሆኑ የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ፍቅሬ አማን ነግረውኛል ብሎ ኢትዮ ኤፍ ኤም ዘግቧል።

በዞኑ የመሸገው የሽፍታ ቡድን ቡድን ዜጎች በብዛት በሚኖሩባቸው አካባቢዎች እየተንቀሳቀሱ የዜጎችን ሕይወት እየቀጠፉ ይገኛሉ ብለዋል፡፡

እነዚህ ታጣቂ ቡድኖች ከአካባቢው ለማጥፋት የጸጥታ አካላት የተጠናከረ ስራ እየሰሩ ቢሆንም በአካባቢው ያለው የጸጥታ አካል በቂ ባለመሆኑ ታጣቂዎቹ ለህብረተሰቡ ብቻ ሳይሆን ለጸጥታ አካሉም ጭምር የስጋት ምንጭ እንደሆኑ ነው የተናገሩት።

አሁን ላይ በዞኑ ያለው የጸጥታ ሁኔታ የሚያሰጋ ባይሆንም ኅብረተሰቡ ግን ስጋት ላይ እንደወደቀ የዞኑ አስተዳዳሪ አክለዋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img